Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና የሻሎም ሄልዝኬር ሶልሽን ኩባንያ መስራችና ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊንታ መሃሪ የህክምና ቁሳቁስ ማምረቻ ፋብሪካ በሀዋሳ ከተማ ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ አስቀጡ !

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና የሻሎም ሄልዝኬር ሶልሽን ኩባንያ መስራችና ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊንታ መሃሪ የህክምና ቁሳቁስ ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ በማስቀመጥ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለፁት በጤና ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ለህክምና የሚያስፈልግ ግብዓት ማግኘት ከባድ በመሆኑ ዜጎች ህይወታቸው አደጋ ውስጥ ሲጥል ቆይቷል በማለት ይህ ፋብሪካ ይህን ችግር የሚፈታ በመሆኑ የክልሉ መንግስት በትኩረት ያየዋል ብለዋል። ፋብሪካው ከአገር ውስጥ አገልግሎቱ በተጨማሪ ወደ ውጭ ኤክስፖርት የሚያደርግ መሆኑ ከውጭ ምንዛሬ አንፃር ፋይዳው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ፋብሪካው እንዲገነባ የበኩላችንን ድርሻ እየተወጣን ቆይተናል በማለት ኩባንያውም በአጭር ግዜ ውስጥ ፋብሪካውን ገንብቶ ወደ ስራ እንዲገባ አሳስበዋል።

የሻሎም ሄልዝኬር ሶልሽን ኩባንያ መስራችና ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊንታ መሃሪ የክልሉ መንግስት ላደረገው ትብብርና ድጋፍ አመስግነው ፋብሪካውን በተባለለት ጊዜ ገንብተን ለመጨረስ እንሰራለን ብለዋል።

የሲዳማ ሒብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ግንቦት 26-2015 ዓ.ም

ሀዋሳ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *