Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ኮሌራ ምንድን ነው?

  1. ኮሌራ ምንድን ነው?

ኮሌራ በአይነምድር እና ትውከት ውስጥ በሚገኙ በአይን በማይታዩ ተህዋሲያን አማካኝነት የሚመጣ ሲሆን ፤ በሰውነት ውስጥ የሚገኘውን ፈሳሽ  

  1. ኮሌራ ምንድን ነው?

ኮሌራ በአይነምድር እና ትውከት ውስጥ በሚገኙ በአይን በማይታዩ ተህዋሲያን አማካኝነት የሚመጣ ሲሆን ፤ በሰውነት ውስጥ የሚገኘውን ፈሳሽ   አሟጦ በማስወጣት አቅምን የሚያዳክም በሽታ ነው፡፡  አፋጣኝ ሕክምና ካልተደረገ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡

  • ለኮሌራ አጋላጭ ሁኔታዎች፡-
  • የተበከለ ውሃ  
  • የተበከለ ምግብ
  • የግል እና የአካባቢ ንፅህና ጉድለት
  • ሜዳ ላይ መፀዳዳት
  • የመፀዳጃ ቤቶችን በአግባቡ አለመጠቀም/አለመኖር
  • የኮሌራ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች
  • በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከለ የምንጭ፣ የጉድጓድ፣ የወንዝ፣ የዝናብ፣ የቧንቧ እና የሀይቅ ውሃን መጠቀም፣
  • በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከለ የውሃ ማጠራቀሚያና መገልገያ እቃዎችን በአግባቡ ሳያፀዱ መጠቀም፣
  • በአግባቡ ባልታጠበ እጅ ምግብን ማዘጋጀት፣ ማቅረብና መመገብ፣
  • በበሽታው አምጪ ተህዋስያን የተበከለ ምግብ፣ አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችን መመገብ፣
  • ክዳን የሌላቸውና ለዝንቦች የተጋለጡ የምግብ ማስቀመጫና መመገቢያ እቃዎችን መጠቀም፣
  • የኮሌራ ታማሚ ተቅማጥና ትውከትን በአግባቡ አለማስወገድ፣
  • ከኮሌራ ታማሚ ጋር ንክኪ የነበራቸው ቁሳቁስ እና ተሸከርካሪዎችን በአግባቡ ሳይፀዱ መልሶ መጠቀም፣
  • በኮሌራ ምከንያት ህይወቱ ያለፈ ሰው አስከሬን ጋር ንክኪ ማድረ
  • የኮሌራ በሽታ መከላከያ መንገዶች
  • ለመጠጥ  የሚውል ውሃን አፍልቶ በማቀዝቀዝ ወይንም በውሃ ማከሚያዎች አክሞ መጠቀም፣
  • ለቁሳቁስ ንፅህና መጠበቂያ የሚውል ውሃን አፍልቶ ወይንም በውሃ ማከሚያዎች አክሞ መጠቀም፣
  • የውሃ ማጠራቀሚያ እቃዎችን ሁልጊዜ በታከመ ወይም በፈላ ውሃ ማጠብ እና መክደን፤ 
  • ንጹህ የማብሰያ ዕቃዎች እና ሳህኖችን መጠቀም፣
  • ምግብን በደንብ አብስሎ በትኩስነቱ መመገብ ፣
  • ሳይበስሉ የሚበሉ አትክልትና ፍራፍሬዎችን በታከመ ውሃ ማጠብና ወዲያውኑ መመገብ፣
  • የተረፉ ምግቦች በዝንቦች እንዳይበከል  መክደን፣ በንፁህ ቦታ  ማስቀመጥ እና ከመመገብ በፊት ማሞቅ/ማንተክተክ
  • ለመብል የተዘጋጁ ምግቦችን ካልተዘጋጁ ምግቦች ለይቶ ማስቀመጥ፣
  • በሚከተሉት ወሳኝ ጊዜያት እጅን በአግባቡ በሳሙና/አመድ እና በንፁህ ውሃ መታጠብ፡
    • ምግብ ከማዘጋጀት በፊት
    • ከመመገብ በፊት   
    • ለሕጻናት ጡት ከማጥባት ወይም ምግብ ከመመገብ በፊት
    • ሕፃናት ካፀዳዱ በኋላ
    • መጸዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ    
    • በኮሌራ ለታመመ ሰው እንክብካቤ ከተደረገ በኋላ
    • በኮሌራ ምክንያት ሕይወቱ ያለፈ ሰው አስክሬን ጋር ንክኪ ከተፈጠረ በኋላ
  • መጸዳጃ ቤቶችን መጠቀም፣ በንጽህና መያዝ እና ከተጠቀሙ በኋላ መክደን
  • የሕጻናትን ዓይነ ምድር መጸዳጃ ቤት ውስጥ መድፋት፣ ወይም ጠለቅ ያለ ጉድጓድ ቆፍሮ መቅበር
  • የታማሚውን ተቅማጥ እና ትውከት በአግባቡ መቀበል፣ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መድፋትና ከጨረሱ በኋላ እጅን በሳሙና እና በውሀ በደንብ መታጠብ
  • ደረቅ እና ፈሳሽ ቆሻሻን በአግባቡ ማስወገድ
  • የበሽታው ምልክቶች
  • በድንገት የሚከሰት ብዛት ያለው አጣዳፊ ውሃ መሰል ተቅማጥ (የሩዝ ውሃ የሚመስል)
  • በተደጋጋሚ ማስመለስ
  • ኮሌራ ትኩሳት ወይንም የቁርጠት ህመም ላይኖረው ይችላል ፤ ይሁን እንጂ ቶሎ ህክምና ካላገኘን በሰውነታችን ያለው ፈሳሽ ተሟጦ ሰለሚያልቅ የአቅም ማነስ ፣ የቆዳ መሸብሽብ ፣ የአይን መሰረጎደ ፣ የአፍ መድረቅ ብሎም ሞት ያስከትላል፡፡
  • በኮሌራ ህመም ወቅት ሊወሰዱ የሚገቡ እርምጃዎች
  • ከምልክቶቹ አንዱ በታዬ ጊዜ ወደ ህክምና ተቋም እስክንደረስ ድረስ ቤት ውስጥ በሚገኘ ማንኛውንም ንጽህናው የተጠበቀ ፈሳሽ መውሰድ ያስፈልጋል
  • .አር.ኤስ በቤት ውስጥ ከሌለ 6 የሻይ ማንኪያ ስኳር እና ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው በአንድ ሊትር ንጹህ ውሃ በመበጥበጥ ባስቀመጥዎ ቁጥር ይጠጡ።
  • ህይወት አድን ንጥረ ነገር ወይም ኦ.አር.ኤስ በቤት ውስጥ ካለ አንድ ፓኬት ተፈልቶ በቀዘቀዘ አንድ ሊትር ውሃ በመበጥበጥ ይጠጡ፤ ኦ.አር.ኤስን መጠቀም የሚቻለው በተበጠበጠ በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ ነው።
  • ጡት የሚጠቡ ህፃናት በበሽታው ከተያዙ ጡት ማጥባትዎን ከወትሮው በመጨመር ይቀጥሉ፣

ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር፡

É7794  ይደውሉ ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *