Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የኮሌራ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በሲዳማ ክልል ተጀመረ

Dr.Damene Debalke

በዛሬው ዕለት በአፍ የሚሰጠው የኮሌራ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በሲዳማ ክልላዊ መንግስት ተፈሪ ኬላ ከተማ በደራ ኦቲልቾ ወረዳ የጤና ሚንስቴር ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር ደረጃ ድጉማ፣ የኢትዮዽያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ እና ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ፣ የደቡባዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳደሪ፣ የወረዳው ጤና ቢሮ ም/ል ሀላፊ፣ የሲዳማ ክልል የሕብረተሰብየሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በይፉ ተጀምሯል።
በዘመቻው ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ላይ እንደተገለፀው በወረዳው 81 ሰዎች በበሽታው ተጠቅተው የነበረ ሲሆን ሁሉም በወረዳው በተቋቋሙት ሶስት የኮሌራ ህክምና ማእከሎች ህክምና አግኝተው በአሁኑ ወቅት በመልካም ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በወረዳው ባለፉት 16 ቀናት በሽታው ሪፖርት አልተደረገም።
በዚህ ዙር እነደሀገር ክትባቱ ከአንድ አመት እድሜ በላይ ለሆኑ 2.3 ሚሊዮን ዜጎች የሚሰጥ ሲሆን በወረዳው የሚሰጠው 90 ሺህ ዶዝ መሆኑ ተገልጿል።
በስነ ስርአቱ መጨረሻም የወረዳው ጤና ጣቢያ ተጎብኝቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *