Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ዛሬ የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሰራውን የሶስት ጥናት ዉጠት  ይፋ አድርጓል።

ታህሳስ 26/2016 ዓ.ም

ሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት

ሀዋሳ

የዕለቱን እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የሲዳማ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ሲሆን በመልዕክታቸው፣ እንዳነሱት ተቋሙ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ አራት ዋና ዋና ሥራዎችን ማለትም ድንገተኛ የጤና አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ፣ ደረጃውን የጠበቀ የላብራቶሪ አግልግሎት ለሁሉም ጤና ተቋማት ማዳረስ ፣ጥራት ያለውን መረጃ በአንድ ቋት ማደራጀት እና ማሰራጨት ፣ የተለያዩ የጥናት እና ምርምር ሥራዎች መስራት መሆኑን ጠቅሶ፣ እነዚህን ተግባራት ተቋሙ ሙሉ አቅም እና ዕውቀት ተጠቅሞ   እየሰራ መቆየቱን ገልፀዋል ።

በመቀጠልም ያደጉ ሀገራት መሰረታቸው ጥናት እና ምርምር በመሆኑ ፣ እኛም የህዝባችንን ችግሮች በጥናት ለይተን  ለመፍታት ሦስት ጥናት ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር መስራት ችለናል ብሏል ። በዚህ መሰረት

1.የቆየ የኩላሊት በሽታ ሁኔታ እና መንስኤዎች/Chronic kidney diseases(CKD) and it’s associated factors in Sidama region.

2.የአኖፊለስ የወባ ትንኝ ስርጭት /invasion of anopheles mosquitoes in Sidama region.

3.የእናቶች ሞት መንስኤዎች /maternal mortality in Sidama region.

ከላይ የተጠቀሱት የሕብረተሰብ ጤና ችግሮችን መነሻ በማድረግ የተሰራው ጥናት መሆኑን ገልፀዋል።

በመቀጠልም የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በበኩላቸው፣ ሥራዎችን በባህላዊ አካሄድ ብቻ ሳይሆን ፣ችግሮቻችንን በጥናታዊ መልክ መስራት የሀገራችን ዕድገት ደረጃ አመላካች መሆኑን ገልፀው፣ እንደዚህ አይነት ጥናት እና ምርምር በሚሰራበት   ጊዜ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ አስፈላጊውን ዕገዛ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል።

በመጨረሻም የእለቱ ክብር እንግዳ የተከበሩ አቶ ተሰማ ዲማ የሲዳማ ክልል የፕሬዝዳንት ልዩ አማካሪ በበኩላቸው ፣ ለዚህ ጥናት እና ምርምር ዋጋ የከፈሉ አካላትን አመስግነው፣ የተሰሩ ጥናቶች የህዝባችን ጥያቄዎችን መሠረት ያደረገ  በመሆኑ ችግር ፈቺ ነዉ  ብለዋል፣ አክለውም የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በቀጣይም እንደዚህ አይነት ጥናቶችን በሚሰራበት ጊዜ የክልሉ መንግስት አስፈላጊ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል።

በዕለት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የክልሉ የቢሮ ሀላፊዎች፣የክልሉ የማህበራዊ ዘርፍ ሀላፊዎች፣የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ መምህራን ፣የጤና ቢሮ ባለድርሻ አካላት፣ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሀላፊዎች ፣ የዞን እና የወረዳ አመራር  በተገኙበት  የጥናት ግኝቶች የቀረቡ

ሲሆን፣ በቀረበው የጥናት ግኝት ዙርያ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ከተነሱ በኋላ ፣ከጥናት አቅራቢዎች እና ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶ የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል።

  የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት

             ሲዳማ/ሀዋሳ

            26/04/2016 ዓ.ም.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *