Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ዛሬ በሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የክልላዊ ጤና መረጃ አስተዳደርና ቅመራ ማዕከል በሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በጤና መረጃ ዘመቻና ትግበራ ላይ የተዘጋጀ አውደ ጥናት ተካሂዷል፡፡

ዛሬ 28/05/2016 ዓ.ም በሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ዳይሮክቶሬት በሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በጤና መረጃ ዘመቻና ትግበራ ላይ የተዘጋጀ አውደ ጥናት (Data campaign and implementation workshop) ተካሂዷል::የዕለቱን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሙንጣሻ ብርሃኑ ናቸው፡፡

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሻግሬ በየነ እንደገለፁት የጤና መረጃ ማዕከል ማቋቋም የመረጃ አጠቃቀም ባህልን በማዳበር በጤና ዘርፍ የሚስተዋለውን የመረጃ ስራዓት ችግር ይፈታል በተለይም በመረጃ ማዕከሉ የጥናቶች ፣ሪፓርቶችና የተለያዩ የጤና መረጃዎችን በማከማቸት ለተለያዩ ስራዎች ማዋል እና መረጃዎችን እንደሃብት መጠቀም በመረጃ ጥራትና ወጥነት ላይ የበለጠ ስራ መስራት እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *