ዛሬ የካቲት 10/2016 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ከሥራ ክፍል ኃላፊዎች ጋር በመቀናጀት በክልሉ ስር ከሚገኙ ከተለያዮ ወረዳዎች የተወጣጡ የጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ከአራቱም ዞን የማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊዎችና የጤና ክፍል ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በቀን የካቲት 10/2016 ዓ.ም በክልሉ የተከሰተው የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ ያለበት ደረጃ ገምግሞ ደካማ ጎኑን በመለየት በቀጣይ ወረርሽኙን ለማስቀረፍ ልሰራባችው የሚገባውን ነጥባች ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
የተወያዩበት አበይት ጉዳዮች፡-
1.ለሕብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ መሆኑ ተጠቅሷል ።
2.ጠንካራ የሆነ ድጋፍና ክትትል መደረግ እንዳለበት በቀጣዩ እንደ መፍተሄ አቅጣጫ ተቀምጧል ።
3.የጤና ባለሙያ አቅም ማጎልበት በዝርዝሩ አቅጣጫ ላይ ተቀምጧል ።
4.ወረርሽኙን ለማስቆም ጠንካራ ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ መቀጠልም እንዳለበት ተገልጿል ።
ምንጭ :- ከሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት
የካቲት 10/2016 ዓ/ም
ሀዋሳ ሲዳማ