Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

Month: March 2024

የጤና መረጃ መኖር ቁልፉ ሚና እንዳለው ተገለጸ፡፡

በጤናው ዘርፍ ለውጤታማ ውሳኔ ሰጪነት ትክክለኛ የጤና መረጃ መኖር ቁልፉን ሚና እንደሚጫወት ተገለጸ፡፡ ዶክተር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስትር የመሠረታዊ የበሽታ ጫና አሰራሮች ስልጠና መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ትክክለኛ የጤና መረጃ መኖር በጤናው ዘርፍ ለሚኖረው ውጤታማ ውሳኔ ሰጪነት የሚጫወት ሚና እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡ ዶክተር ሊያ አያይዘውም የበሽታዋችን ጫና ለመቀነስ መረጃዎችን በመጠቀም ውጤታማ የጤና ውሳኔዎችን…
Read more

7794

ከክፍያ ነጻ የስልክ መስመር በመጠቀም ድንገተኛ አደጋዎች ሲያጋጥመዎ ጥቆማ ይስጡ !! በሲዳማ ክልል ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት የካትት 24/2016 ዓ.ም ሲዳማ/ሀዋሳ

የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት በዛሬው ዕለት የኩፉኝ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ረገድ በወሬዳዎች የምገኙ የጤና አ/ጣቢያ ኃላፊዎች ፣ IDSR focal እና በጤና ተቋማት ተመላላሽ ህክምና ክፍል ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ።

ጤናማ ፣ አምራችና የበለጸገ ህብረተሰብ ለመፍጠር እንቅፋት የሚሆኑ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች እና የተከሰተው የኩፉኝ ወረርሽኝ ስለመተላለፊያ መንገዶችና የመከላከያ ስልቶችን አስመልክቶ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ፤ ለተሳታፊዎች የተከሰተው ወረርሽኝ ለመከላከል በተቀናጀ መልኩ ሊመራ እንደሚገባ የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ አሳሰቡ። በመጨረሻም ከሰልጣኞች የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተነስተው ለተነሱ…
Read more

የጊኒዎርም በሽታን ተባብረን እናጥፋ

28ተኛዉ አገር አቀፍ የጊኒዎርም በሽታ ዓመታዊ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የካርተር ሴንትር፣ የአለም ጤና ድርጅት እና የክልሎች ጤና ቢሮ እንዲሁም ሌሎች አጋር አካላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ለሁለት ቀናት በሚካሄደው የምክክር መድረክ ላይ በዓመቱ ዉስጥ የተከናወኑ በርካታ ሥራዎች አፈጻጸም የሚቀርብበት፣ የሚገመገምበት እንዲሁም ዉይይት የሚካሄድበት እና…
Read more

ዓመታዊ የጸረ-ተህዋስያን መድሃኒቶች ብግርነት የዳሰሳ ጥናት የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ነው

በኢንስቲትዩቱ የባክቴሪያል፣ የፓራሳይቲክ እና እንሰሳት ነክ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ እና ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም ም/ዋና ዳይሬክተሮች በተገኙበት ዓመታዊ የጸረ-ተህዋስያን መድሃኒቶች ብግርነት Ani-microbial Resistance (AMR) የዳሰሳ ጥናት የምክክር መድረክ የካቲት 18 እና 19/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ የምክክር መድረኩ ዋና ዓለማ ኢ.ኤ.አ…
Read more

የክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ሽኝት እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ፡፡

የክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ሽኝት እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት የክልል ጤና ቢሮ የስራ ኃላፊዎች የተጠሪ ተቋማት፣ የጤና ሚኒስቴር እንደዚሁም የፌድራል እና በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ስር የሚገኙ የሆስፒታሎች ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በደማቅ ሁኔታ አከናውነዋል፡፡ በመድረኩ ሽኝት የተደረገላቸው ክብርት ዶ/ር ሊያ በጤና ሚኒስትርነት ሃገራቸውን በማገልገል ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጾ እና በጤናው ዘርፍ መሪነት ላስመዘገቧቸው…
Read more

የጤናውን ሴክተር አንድ እርምጃ ወደፊት ሊያራምደው የሚችል ለበሽታ ቅኝትና ምርምር አገልግሎት የሚውል የተቀናጀ የተላላፊ በሽታ ተዋስያን የዘረ-መል ምርመራ እና ባዮኢንፎርማቲክስ ፕሮግራም ስራ ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ፡፡

————————— ክቡር ዶ/ር አየለ ተሾመ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ በዛሬው እለት በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የስብሰባ አዳራሽ በመገኘት በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ይህ ለጤናው ሴክተር ትልቅ እገዛ ሊያደርግ የሚችለው ፕሮግራም መጀመርና የክፍሉ መቋቋም በሀገር አቀፍ ደረጃ የማሕበረሰብ ጤና እርምጃዎች መረጃን ለማመንጨት እና ለመተንተን ብሎም ለመተርጎም፣ ለመጠቀም እና ለማጋራት እንደሚያስችል አስረድተዋል። ክቡር የጤና ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘውም…
Read more