Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት በዛሬው ዕለት የኩፉኝ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ረገድ በወሬዳዎች የምገኙ የጤና አ/ጣቢያ ኃላፊዎች ፣ IDSR focal እና በጤና ተቋማት ተመላላሽ ህክምና ክፍል ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ።

ጤናማ ፣ አምራችና የበለጸገ ህብረተሰብ ለመፍጠር እንቅፋት የሚሆኑ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች እና የተከሰተው የኩፉኝ ወረርሽኝ ስለመተላለፊያ መንገዶችና የመከላከያ ስልቶችን አስመልክቶ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ፤ ለተሳታፊዎች የተከሰተው ወረርሽኝ ለመከላከል በተቀናጀ መልኩ ሊመራ እንደሚገባ የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ አሳሰቡ።

በመጨረሻም ከሰልጣኞች የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተነስተው ለተነሱ ጥያቄዎች በዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዳመነ ደባልቄ ምላሽ ከተሰጠ በኃላ፣በቀጣይ መጠናከር ያለበት ሥራዎች ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።

የሲዳማ ክልል ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት

የካቲት 23/2016 ዓ.ም

ሀዋሳ/ሲዳማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *