Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ሽኝት እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ፡፡

የክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ሽኝት እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት የክልል ጤና ቢሮ የስራ ኃላፊዎች የተጠሪ ተቋማት፣ የጤና ሚኒስቴር እንደዚሁም የፌድራል እና በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ስር የሚገኙ የሆስፒታሎች ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በደማቅ ሁኔታ አከናውነዋል፡፡

በመድረኩ ሽኝት የተደረገላቸው ክብርት ዶ/ር ሊያ በጤና ሚኒስትርነት ሃገራቸውን በማገልገል ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጾ እና በጤናው ዘርፍ መሪነት ላስመዘገቧቸው ውጤቶች ምስጋና እና እውቅና ተችሯቸዋል፡፡ ክብርት ዶ/ር ሊያ ከአመራር ሚናቸው በተጨማሪ ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን የድንገተኛ የማህበረሰብ ጤና ስራዎችን በቅንጅት ምላሽ ከመስጠት አኳያ እንደዚሁም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶች ሳይቋረጡ በማስቀጠል ረገድ ጉልህ እና የማይተካ አስተዋጽኦ ያበረከቱ መሆናቸው በመድረኩ ተገልጿል፡፡

ለተደረገላቸው የእውቅ ስነ ስርዓት ምስጋና ያቀረቡት ዶ/ር ሊያ በጤና ሚኒትርነት በነበራቸው ጊዜ ከጎናቸው በመቆም ድጋፍ ላደረጉላቸው ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የስራ ባልደረቦቻቸው፣ ባለድርሻ እና አጋር አካላት እንደዚሁም መላ ቤተሰባቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ባለፉት አመታት የጤናው ዘርፍ ገጥሞት ከነበረው የኮቪድ 19 እና ሌሎች ተግዳሮት መሻገር የተቻለው የጤና ሚኒስቴር ሰራተኞች፣ የክልል ጤና ቢሮዎች፣ ተጠሪ ተቋማት እና አጋር ድርጅቶች በአንድነት በመጣመር በቡድን መንፈስ መስራት በመቻላቸው መሆኑን ዶ/ር ሊያ አክለው ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ የጤና ሚኒስትርነት ሚናን በይፋ የተረከቡት ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስቴር ሰራተኞች እና አመራሮችን ተዋውቀዋል፡፡ ሚኒስትር መቅደስ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር በጤና ሚኒስቴር እንደ ባህል የተያዘውን የቡድን ስራ መንፈስ ማስቀጠል ላይ አጽእኖት ሰጥተዋል፡፡

በጤናው ዘርፍ የመዘገቡ ውጤቶችንም ለማዝለቅ በሙሉ አቅማቸው ከሁሉም ባልደረቦቻቸው እንደዚሁም ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ዶ/ር መቅደስ በመድረኩ ተናግረዋል፡፡

በየሽኝት ሥነ- ሥርዓት ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች፣ የሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች፣ የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ ሄልዝ ኬር ፌዴሬሽን ኃላፊዎች ፣ የጅማ ዩንቨርስቲ የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ሽኝት ሲደረግላቸው ለጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ደግሞ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማሕበራዊ ልማት፣ ባሕልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ እንደተናገሩት ክብርት ሊያ ታደሰ በአመራር ክዕሎታቸው፣ በትህትናቸውና ሰው በማዳምጥ ብቃታቸው ከአገር አልፈው ለመላው አለም ላሉ ሴቶች አርአያ መሆን እንደሚችሉ ጠቁመው ከእሳቸው ጋር በነበራቸው የስራ ግንኙነት ስራን በቅልጥፍናና በውጤታማነት ከሚሰሩ ሴት አመራሮች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል፡፡

በእነዚህ ደማቀ ሽኝትና አቀባበል ሥነ-ሥርዓት ላይ የተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ለክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ በጤናው ዘርፍ በቆዩባቸው አምስት አመታት ላሳዩት በሳልና ቁርጠኛ አመራር እንዲሁም ላስመዘገቧቸው ከፍተኛ አስተዋፆዎች ምስጋና ተችሯቸዋል።

የክልል ጤና ቢሮዎች፣ የተጠሪ ተቋማት፣ የጤና ሚኒስቴር ማኔጅሜን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *