Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ለድንገተኛ ክስተቶች ዝግጁ የሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ተቋማት የመፍጠር ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

የሲዳማ ክልል ሕ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ‘Resolve to save life Ethiopia’ ከተባለ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር በክልሉ ዉስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ ድንገተኛ ክስተቶችን በአግባቡ በመቃኘት፣በጊዜ በማሳወቅና ምላሽ በመስጠት የህ/ሰባችንን ጉዳት የመቀነስ አቅም ማሳደግ እንዲሁም የጤና ተቋማትን ፅዳት በማሻሻል ሊከሰቱ የሚችሉ ብክለቶችን ለመቀነስ ታቅዶ ነዉ ፕሮጀክቱ ይፋ የተደረገዉ።

ፕሮጀክቱን ይፋ ማድረጊያ መድረክ ላይ ንግግር በማድረግ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ሕ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቀ በክልላችን ድንገተኛ ክስተቶችን ቀድሞ በመከላከልና ከተከሰቱም ፈጣን ምላሽ በመስጠት በርካታ ስራዎችን በመስራት እንደ ክልል አበረታች ዉጤቶች እንደተገኙ ገልፀዉ ይህንን ዉጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ተቋማትን አቅም የበለጠ ለማጠናከር ወሳኝ ፕሮጀክት በመሆኑ የሚመለከታቸዉ አካላት ለተግባራዊነቱ ተገቢዉን ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

በመድረኩ ከ Resolve to save life Ethiopia፣ከወረዳ፣ከዞን፣ከከተማና ከአኢንስቲትዩቱ ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ አካላት ተሳትፈዋል።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ሚያዚያ 4/2016 ዓ.ም

ሀዋሳ/ሲዳማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *