Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

በሲዳማ ብ/ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ March-8 ቀን ተከበረ!

በዓለም ለ113 ፣ በሀገራችን ደግሞ ለ48 ጊዜ ”የሴቶችን አቅም በማጎልበት የጤና ልማትን እናፋጥን ” በሚል መሪ ቃል የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ፣ የጤና ቢሮና የተጠሪ ተቋማት ማኔጅመንትና ሰራተኞች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በመድረኩ ላይ የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በንግግራቸው የሴቶች ሁሌንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም በትኩረት ሊሰራ ይገባል፤ ሴቶች በቤተሰብ ደረጃ ፣ በማህበረሰብና በሥራ ቦታ ሊሰጣቸው የሚገባውን ክብርና ሊያገኙት የሚገባውን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ እና የወንዶችን አጋርነት በሚፈጥር ሁኔታ በዘወትር እንቅስቃሴችን ደረጃ ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ ቀርቦ ውይይት በማድረግ በቢሮ ኃላፊዋ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ

መጋቢት 6/2016 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *