Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

በሲዳማ ክልል ”ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን ለውጡን እናጸናለን! ” በሚል መሪ ቃል የለውጡን መንግስት ስድስተኛ ዓመት የሚደግፍ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ አካል የሆነው የክልሉ ማዕከል መ/ቤቶች ሠራተኞች ፣ ሰሜናዊ ዞን እና ሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎችን ያካተተው በዚህ ሰዓት በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል ።

. የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከያዟቸው መፈክሮች ከለውጡ ወዲህ የተገኙ ድሎችን የሚወድሱ እና ከለውጡ ወዲህ በአገሪቱና በክልሉ የተመዘገቡ የልማትና የዴሞክራሲ ግንባታ ውጤቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መንግስትን የሚደግፍ ዓላማ ያነገበ ነው።

ከመፈክሮቹ ለመጥቀስ ያህል :-

1. እኛ ኢትዮጵያውያን ለሀገራችን ሠላምና ሁለንቴናዊ ብልፅግና የበኩላችንን እንወጣለን !!

2. የላቀ ህዝባዊ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ብልፅግና !!

3. ሀገራችንን ወደ ከፍታ ለማሻገር ከለውጡ አመራር ጋር በፅናት እንቆማለን !!

4.ያሰበውን የሚሠራ የጀመረውን የሚጨርስ መንግስት አለን !!

5. ለሀገራችን ሰላምና አንድነት የማንከፍለው ዋጋ አይኖረንም !!

ወዘተ… መፈክሮች ይገኙበታል ::

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮና የተጠሪ ተቋማት ሠራተኞችም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እጅግ ባሸበረቀ መልኩ ይህንን የድጋፍ ሰልፍ በግንባር ቀደሚትነት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

መጋቢት 30/2016 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *