Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች በሲዳማ ክልላዊ መንግስት የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የስራ ልምድ ልውውጥ አደረጉ ።

በልምድ ልውውጡ በክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዮት እየተተገበረ ያለውን የመረጃ አያያዝ /ዳታ ማናጅመንት ሲስተም ፣ የነፃ ስልክ ጥሪ ማእከል (call centre) ፣ የሕብረተሰብ ጤናና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር (PHEM) ፣ የክልል ላቦርቶሪ (Regional Laboratory) እና የሕብረተሰብ ጤና ምርምር ስራዎች ላይ የገለጻ እና የአካል ምልከታ በማድረግ የእርስ በዕርስ የአሰራር ልምዶችን በመለዋወጥ በጤናው ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጥራት እና ቅልጥፍና በመጨመር ለተገልጋዩ ወቅቱ የሚጠይቀውን አሰራር ፈጥኖ ለመተግበር እንደሚያስችል ተጠቁሟል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ምርምር እና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ዳምጠው በሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያየናቸውን የአሰራር ልምዶች ወደራሳችን በመተግበር እንዲሁም እኛጋ ያሉትን ደግሞ በማካፈል ልምድ ማግኘት የተቻለ መሆኑን ገልጸው ልምድ ልውውጡ መልካም ግንኙነትን በማጠናከር ለጤናው ዘርፍ ውጤታማነት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የእቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ስምአነሰው በበኩላቸው በክልሉ ለተደረገው መልካም አቀባበል በቢሮ እና በተሳታፊዎቹ ስም አመስግነው ከላይ እስከታች ያለው አመራር እና ባለውያ ስራውን በእኩል ደረጃ አውቆ እና ተናቦ እየተሰራ መሆኑን በተደረገው የልምድ ልውውጥ ማየት መቻላቸውን እንዲሁም ስራዎችን ለማስረዳት ያደረጉትን ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል ።

በሲዳማ ክልላዊ መንግስት የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶክተር ዳመነ ደባልቄ በበኩላቸው ልምድ ልውውጡ የጋራ መማማርን የፈጠርንበት በመሆኑ እኛጋ ያለውን ያካፈልንበት ብቻ ሳይሆን ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮም በርካታ አዳዲስ አሰራሮችን የተረዳንበት እና ይህንንም በአካል ተገኝተን የምናይበትን ሁኔታ እንድናስብ አድርጎናል ብለዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *