Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዮኒኬሽን ባለሙያዎች ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ ተገhፀ ።

የኢትዮጵያ የሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት በአንድ ጤና መርሀ ግቡር (0ne Health) ዙሪያ ለሚሰሩ ለልዩ ልዩ መንግስታዊ ተቋማት መጋቢት 24 እና 25 2016 ዓ.ም ባዘጋጀው “የሕብረተሰብ ጤና ስጋት ተግባቦትና እና የማህበረሰብ ተሳትፎ” ላይ ባተኮረው አውደ ጥናት ላይ የኢትዮጲያ የሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብቴ ባስተላለፉት መልዕክት በአሁኑ ጊዜ የጤና ጉዳይ በርካታ ተቋማትንና አካላትን የሚመለከትና የሚያሳትፍ በመሆኑ ሁሉም ጉዳይ የሚመለከተው ተቋማትና አካላት በጋራ ተባብረው እና ተናበው መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል ። ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች የቅድመ መከላከልም ሆነ የድህረ መከላከል ሥራዎች ለማከናውን የተግባቦት ሙያ የሚጫወተው እገዛ ከፍተኛ በመሆኑ ማህበረሰቡ ጤናው ተጠብቆ አምራች ዜጋ መሆን ይችል ዘንድ ከተግባቦት ባለሙያዎች ህቡረተሰቡን በማስተማርና በማሳወቅ ጉልህ ሚና እንደሚጠበቅ ጠቅሰው በቀጣይም ኢንስቲትዩቱ ከሁሉም ተቋማት ጋር በቅርበት በመስራቱ በኩል በርካታ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ገልፀዋል ::

ዶ/ር ፈይሣ ረጋሣ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ጤና ደህንነት መርሀ ግብር ተጠሪ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት የሀገራችን የጤና መርሀ ግብር ውጤታማ ይሆን ዘንድ ሁሉም ተቋማት እያደረጉ ያለዉን ቅንጅታዊ ሥራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበው በተለይ ትክክለኛ መረጃን በወቅቱ ለማህበረስቡ በማድረስ ረገድ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች ድርሻ ጉልህ በመሆኑ የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅዖ ለማበርከት ይችሉ ዘንድ ይህ ሙያዊ ስልጠና አቅም እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል ።

የህብረተሰብ ጤና ስጋት እና የማህበረሰብ ተሳትፎን አስመልክቶ በተለያዩ አሰልጣኝ ባለሙያዎች ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በመጨረሻም የቀጣይ ስራዎችን በተመለከተ ሰፊ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ::

የጤና ሚኒስቴር ፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ፣ የኢትዮዽያ ግብርና ባለስልጣን ፣ የኢትዮዽ ያ የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ፣ እንስሳት ጤና ኢንስቲትዩ ፣ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የህዝብ ግንኙነት ና ኮሚኒኬሽን ኃላፊዎችና ተወካዮች በስልጠናው ላይ ተሳታፊ ሆነዋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *