Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2016 በጀት አመት የ9 ወር የኤች አይ ቪ ቅኝት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በይርጋዓለም ከተማ እየገመገመ ይገኛል።

የመክፈቻ ንግግር በማድረግ የውይይት መድረክ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙንጣሻ ብርሃኑ የኤች አይ ቪ ሥርጭትን ለመግታት እየተሰሩ ያሉ የቅኝት ሥራዎች አበረታች መሆኑን ጠቅሰው በተለይ ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰብ አባላት ላይ የበለጠ ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት እንደሚጠብቅ አሳስበዋል።

በመቀጠልም የ9 ወር የኤች አይ ቪ ሰርቪላንስ ሪፖርት ዶ/ር አፌንሻ አመሎ ካቀረቡ በኋላ ጠንካራ ውይይት በማድረግ ጥንካሬና ክፍተት በመለየት ቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ ለመደገፍ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት

ሚያዝያ 03/2016 ዓ.ም

ሀዋሳ፣ ሲዳማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *