Skip to content ለኢንስቲትዩቱ በህግ ከተሰጡት ተግባራት መካከል በክልሉ የሚስተዋሉ ዋና ጤና ችግሮች ዙሪያ ሳይንሳዊ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ በግኝቶቹ መነሻ የመፍተሄ ሀሳቦችን መጠቆም ይገኝበታል። በዚሁ መሰረት በያዝነዉ አመት በተለያዩ ጤና ችግሮች ዙሪያ ልዩ ልዩ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በተጠናከረ ሁኔታ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ከምርምር ስራዎቹ መካከል አንዱና ልዩ ትኩረት የተሰጠዉ በክልሉ የመጸዳጃ ቤት ተደራሽነትና ከአጠቃቀም ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ የሚካሄደዉ ጥናትና ምርምር ስራ ሲሆን ምርምሩ ሲጠናቀቅ ግኝቱ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የጎላ ሚና እንደሚኖረዉ ይገመታል።
የስልጠና መድረኩን ንግግር በማድረግ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ሕ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዪት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ እንደገለፁት የሕ/ሰባችንን ጤና ለማሻሻል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በሳይንሳዊ ጥናይና ምርምር መደገፊ እንዳለባቸዉ ገልፀዉ ይህንን ለማድረግ የሕ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል። አክለዉም የጥናትና ምርምር ስራዉን ዉጤታማ ለማድረግ የመረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣሪዎች ሚና የጎላ በመሆኑ በልዩ ትኩረትና ጥንቃቄ እንዲሰራ አሳስበዋል።
በስልጠና መድረኩ ላይ ከክልሉ ጤና ቢሮ ፣ከሕብረተሰብ ጤና ኢንሰእቲትዩና ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተመራማርዎች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸወኡ አካላት ተገኝተዋል።
የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሀዋሳ/ሲዳማ
ሚያዝያ 1/2016 ዓ፡ም
- by admin
- on April 15, 2024
0