Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

በሲዳማ ብ/ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በዛሬው ዕለት ለጤና አመራሮችና ለጤና ተቋማት ኃላፊዎች ”ብቁ የጤና አመራር ለላቀ ውጤት እና ጥራት ” በሚል መሪ ቃል ለሶስት ቀናት የሚሰጠው ስልጠና ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ ::

በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አብርሃም ማርሻሎ በንግግራቸው ከሁለት ዓመት በፍት በጤና ሴክተር ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚያያዙ ፣ የግብዓት አቅርቦት ፣ አያያዝ እና መሰል ችግሮች እንደነበሩ ገልጸው የጤና ቢሮው አመራሮች ቆም ብለው የችግሩን ምንጮችና የመፍትሄ አቅጣጫን መቀየስ በመቻላቸው በአሁኑ ጊዜ በሴክተሩ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል :: ኃላፊው ለመጣው ውጤት የድርሻቸውን የተወጡ የሴክተሩን መዋቅሮች አመስግነው አሁንም ግን በሚፈለገው መልኩ በተለይም የመሪነት ሚናቸውን በአግባቡ ከመወጣት አኳያ ጉድለት የሚታይባቸው እንዳሉም ጠቁመው ስልጠናው ጉድለቱን ከመዝጋት አኳያ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይታሰባል ብለዋል።
ከስልጠናው በኋላ ሁሉም መዋቅሮች ሞዴል ቀበሌያትንና ወረዳዎችን ለመፍጠር ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባም አቶ አብርሃም አሳስበዋል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በበኩላቸው በጤናው ሴክተር ይታዩ የነበሩ የአሠራርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ የአለም ጤና ድርጅት ካወጣቸው ስድስቱ መሠረታዊ ዋልታዎች አኳያ ተፈትሸው ከተለዩ በኋላ ”ለላቀ ውጤት እንስራ ” በሚል መሪ ቃል በተሰራው ሥራ በአሁኑ ጊዜ የተሻለ ውጤት ቢመዘገብም ሁሉንም ጤና ተቋማትን ከማመጣጠን አኳያ የሚታዩ ጉድለቶችን ለመዝጋት በዛሬው ዕለት ”ብቁ የጤና አመራር ለላቀ ውጤትና ጥራት ” በሚል መሪ ቃል ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጸው ሰልጣኞቹ በክልሉ በተለዩ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የሚሰጠውን ስልጠናውን በአግባቡ መከታተል እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመድረኩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አክቡር አቶ አብርሃም ማርሻሎ ፣ የክልሉ የብ/ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ አሸናፊ ኤልያስ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት እና የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች ፣ የዞን አስተዳዳሪዎችና የፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ የዞን ማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊዎች
የወረዳ አስተዳዳሪዎች ፣ ዞኖች ጤና ዴስክ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ፣ የወረዳ ዋና እና ምክትል ኃላፊዎች ፣ የሁሉም ሆስፒታል እና የጤና ጣቢያ ኃላፊዎችና እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተሳትፈዋል።
በመጨረሻም የስልጠናውን አስፈላጊነት እና ሌሎች የጋራ አጀንዳዎች ዙሪያ ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ሰነዶች እየቀረቡ ይገኛል ።
የስዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ግንቦት 27/2016 ዓ.ም
ምንጭ:-የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ድረገጽ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *