Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

” ብቁ የጤና አመራር ለላቀ ውጤት እና ጥራት ” በሚል መሪ ቃል በሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ አዘጋጅነት ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በማጠቃለያ መድረክ ላይ ባስተላለፉት መልዕክታቸው ስልጠናው አንድ የጤና አመራር /ባለሙያ ሊጠብቀውና ሊተገብረው የሚገባውን ወሳኝ የሆኑ የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን አውቆ እንዲተገብር የሚያስችል ነው።
ከዚህ አኳያም ባለፉት ሶስት ቀናት የተሰጠው ስልጠና ውጤቱ ቀጥሎ በእያንዳንዱ መዋቅር ደረጃ በሚኖረው አፈጻጸም የሚለካ ሆኖ ሰልጣኙ ወደ መደበኛ ሥራ ቦታቸው ሲመለሱ ከዚህ በፍት ከነበረው በተሻለ ሁኔታ የአሰራር ስርዓቱን ጠብቆ መምራት ያስችላቸዋል ተብሎ ይታመናል። ውጤቱ የሚለካው ደግሞ ወረዳውን ሞዴል አድርጎ የማውጣት/አለማውጣት ጉዳይ እንደሆነም ገልጸዋል።
የቢሮ ኃላፊዋ አያይዘውም ”ለውጤት /ለላቀ ውጤት እንስራ” ብለን ከጀመርን ጀምሮ የማህበረሰባችንን ችግር ለመቅረፍ በተሰሩ ስራዎች የመጣውን ውጤት ማየት መጀመራችን እንደተጠበቀ ሆኖ በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ ”ለላቀ ውጤት እና ጥራት ” ለመሥራት ቢሮው ቅድመ ዝግጅቱን በስልጠና መጀመሩ በሀገር ደረጃ እና በክልላችን ለሚተገበረው ለዕድገትና ኢንቬስትመንት ዕቅድም ትግበራ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል።
በመጨረሻም ቀሌያትንና ወረዳን በቁጥር ሞዴል ከማድረግ ባሻገር የማህበረሰባችንን ጥያቄ በመፍታት፣ በአግባቡና በጥራት በማገልገል የህዝባችንን ጥያቄ የሚመልስ ስራ ልንሰራ ይገባል ሲሉ ዶ/ር ሰላማዊት በአጽንኦት ገልጸዋል።
በዕለቱም የደም ልገሳ በጎ ተግባርም ተከናውኗል።
የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት
ግንቦት 29/2016 ዓ.ም
ምንጭ:-የስዳማ ክልል ጤና ብሮ ድረ ገጽ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *