Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ”National Information Platform Nutrition (NIPN)” ፕሮጀክት ጋር በትብብር ለመስራት የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ፤

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፕሮጀክቱን ወደ ሲዳማ ክልል አውርዶ ለመስራት ግንቦት 22 /2016 ዓ.ም በሀዋሳ በተዘጋጀው ወርክሾፕ ላይ የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል።
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር መሳይ ኋይሉ በስምምነቱ ላይ እንደናገሩት ፕሮጀክቱ ከስርዓተ – ምግብ ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን ችግር በምርምር ለመፍታት የሚሰራ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ የተቀበለውን ሃላፊነት በተሻለ ደረጃ እየተወጣ እና ወደ ክልሎች ለማድረስ እየሰራ ነው ብለዋል።
የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የስዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት ለማጠናከር እየሰራ ያለው ስራ ጥሩ መሆኑን ገልፀው ፕሮጀክቱ ክልሉ አብሮ እንዲሰራ እድሉ በመፈጠሩ ምስጋና አቅርበዋል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክልሉ ከሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ የመስራት ፍላጎት እንዳለው ያስረዱት ዶ/ር ዳመነ የክልላችንን የስርዓተ – ምግብ ችግር ለመፍታት ልዩ ትኩረት ሰጥተን ተቋማትን አቀናጅተን በመስራት ውጤት እናመጣለን ብለዋል።
በመድረኩ የፕሮጀክቱ አስተባባሪና መሪ ተመራማሪ ዶ/ር አረጋሽ ሳሙኤል በፕሮጀክቱ የሚከናወኑ ተግባራትን ያቀረቡ ሲሆን መረጃን መሰረት ያደረገ ውሳኔ እንዲሰጥ ተመራማሪዎችንና ውሳኔ ሰጪ አካላትን ማገናኘት የፕሮጀክቱ ዓላማ እንደሆነ አስረድተዋል።
ዶ/ር አረጋሽ አክለውም ፕሮጀክቱን ወደ ሲዳማ ክልል በማውረድ ወደ ስራ ለማስገባት እንደሆነ ገልፀው ከዝህ በፊት ብዙ ውጤት እንደመጣ ገልፃ በሲዳማ ክልልም ጥሩ ውጤት እንድመጣ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ተቋማት በቅንጅት በመስራት ሃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተቀበለውን ሃላፊነት መፈፀም እንደምችል እምነት እንዳላቸው የተናገሩት ዶ/ር መሳይ በጋራ በመስራት ለክልልም ሆነ ለአገር የሚጠቅም ስራ መስራት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
በመጨረሻም በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር መሳይ ኃይሉ እና የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡
የስዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት
22/09/2016 ዓ.ም
ሲዳማ/ሀዋሳ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *