Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች በዛሬው እለት ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ አካሂደዋል ።

ሳምንታዊው የጽዳት ዘመቻውን ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፍ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ሲሆኑ ዛሬ የሚደረገው የጽዳት ዘመቻ ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት በሳምንቱ መጨረሻ አርብ አርብ ይደረግ የነበረው ዘመቻ መሆኑን ገልጸዋል።
የጽዳት ዘመቻውን በተመለከተ የቢሮ ኃላፊዋ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ንግግር አድርገው ያስጀመሩ ሲሆን በመልዕክታቸውም የዛሬውን የጽዳት ዘመቻ ለየት የሚያደርገው ቁርኝታችንን እና አንድነታችንን ባጠናከረ መልኩ የጤና ስራ አጋሮቻችን ፣ ለስራ ጉዳይ ወደ ቢሮአች የመጡ የፌዴራል ጤና ሚ/ሰራተኞች፣ የጤና ቢሮ ተጠሪ ተቋማት ይህንኑ ስራ የጋራ ለማድረግ ተጋብዘው የመጡ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፣ ሰራተኞቻቸው ፣ የኢንስቲትዩቱ እና ሰራተኞቹ ፣ የጤናና ጤና ነክ የግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ኃላፊዎችና ሠራተኞች በጊብያችን ውስጥ አብረውን ያሉ አጋሮቻች እና የWHO ተወካዮች የተገኙበት መሆኑን ተናግረው ከአንድ አመት በፊት ለውጤት እና ለላቀ ውጤት እንስራ ኢንሸቲቪ በቢሮ ተጀምሮ እየተሰራበት ያለ እና ውጤት የመጣበት መሆኑን አብራርተው ፤ አያይዘውም በዘንዲሮው የአሥር ወር አፈጻጸም እንደ ክልል መንግስት ምዘና የክልል ጤና ቢሮአችን በሶስተኛ ደረጃ ላይ መሆናችንን እና ደረጃውም ሊያኮራን የሚገባ ነው ብለዋል።
ለዚህ ውጤት ጠዋትና ማታ ሳይሉ የደከሙ የቢሮአችን አመራሮችን እና ሰራተኞቹን እጅግ በጣም አመሰግነው በቀሩን ጊዜያት ጠንክረን ከሠራን የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚንችል ገልጸው ለዚህ በቅንነት ያለንን እውቀትና እምቅ አቅማችንን ከተጠቀምን ታርክ መሥራት እንችላለን ብለዋል ።
የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ
ግንቦት 16/9/2016

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *