Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ትላንት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት መሬት ተንሸራተዉ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ፤ ሀምሌ 22/2016

ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳ ግሽሬ፤ጉዱሞና ሆሞ ተብሎ የሚጠራ አከባቢ ትናንት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት መሬት በመንሸራተቱ የ11 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ስድስት ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የክልሉ መንግሥት ከዞን አስተዳደር ጋር በመሆን አደጋ ከደረሰ ስዓት አንስቶ ለዜጎች ተጨማሪ አደጋ ኢንዳያደርስ የማድረጉ ስራና ተጎጂዎች ህክምና እንዲያገኙ አድረጓል።
የክልሉ መንግሥት ተጨማሪ ድጋፊዎችን ለማድረግ የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣የፀጥታ ሀይል እና የሰዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት Emergency Rapid Response team ወደ ስፍራው ተሰማርተዋል ።
ክልሉ መንግሥት በአደጋው ለጠፋው ለሰዉ ህይወት ጥልቅ ሃዘን የተሰማዉ መሆኑን እየገለጸ ለተጎጅ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል።
በሌሎች አከባቢዎችም መሰል ችግሮች ሊፈጠሩ ስለሚችሉ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የክልሉ መንግሥት ጥንቃቄ መልዕክት ያስተላልፋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን እየተከታተልን የሚናቀርብ መሆኑን እንገልፃለን።
ምንጭ
የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *