Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

በሲዳማ ብ/ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የወባ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የሚደረግ የህዝብ ንቅናቄ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የሲዳማ ብ/ክ/መ/ጤና ቢሮ ፤ ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም

  በሀገርቱ ከተፈጠረው የአየር ንብረት መዛባት ጋር በተያያዘ በክልላችንም በአንዳንድ አከባቢዎች የወባ በሽታ ጫና እየተፈጠረ ስለሚገኝ የመከላከሉን ስራ ከወራት በፍት ተጀምሮ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
በዚሁ መሠረት በዛሬው ዕለትም በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ውኃን ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰስና የማዳፈን (የአከባቢ ቁጥጥር ) ሥራ በሕዝብ ንቅናቄ ተደርጓል።
በህዝብ ንቅናቄ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመኔ ደባልቄ ታምሞ ከመማቀቅ አስቀዲሞ በሽታን መከላከል ባህል ሊናደርገው ይገባል ብለዋል ። ኃላፊው አያይዘውም ዛሬ በንቅናቄ ከተሰራው ከአከባቢ ቁጥጥር በተጨማሪ ህብረተሰባችን ሌሎች የወባ መከላከያ ስልቶች ፤ በኬሚካል የታከመ የአልጋ አጎበር አጠቃቀም ፣ የኬሚካል ርጭት እና የወባ ህመም ስሜት የሚታይባቸው ሰዎች ፈጥነው ወደ ህክምና ተቋማት በመሄድ ምርመራና የሕክምና አገልግሎቶችን በማግኘት የወባ በሽታን መከላከልና መቆጣጠር እንደሚገባ ሥራ እንዲተገብርም አሳስበዋል ።
በሌላ በኩል ኃላፊው የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ በክልሉ ከሚገኙት 23 ወባማ ወረዳዎች አንዱ ከፍተኛ የወባ ተጠቂ ህብረተሰብ የሚገኙበት መሆኑን በመጠቆም የመከላከያ ስልቶችን ቀጣይነት ባለው መልኩ ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።
በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የማህበራዊ ዘርፊ አስተባባሪ ወ/ሮ ድንቅነሽ ደግፌ በበኩላቸው በዞኑ ከሚገኙት ወረዳዎች አብዘኛዎቹ ወባማ በመሆናቸው በህዝብ ንቅናቄ የታገዘ የመከላከል ሥራ እየተሰራ ቢሆንም የወባ በሽታ ጫና በሚፈለገው መልኩ እየቀነሰ ባለመሆኑ ሁሉንም የመከላከያ ስልቶችን አቀናጅቶ መተግበር እንደሚገባ ተናግረዋል።
የወረዳው ም/አስተዳዳሪ አቶ ዴአ ሳሳሞ በዕለቱ የተጀመረውን ንቅናቄ ቀጣይነት ባለው መልኩ የወረዳውን ህብረተሰብ በማንቀሳቀስ እንደሚስቀጥሉ ተናግረዋል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም ፤ ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *