Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት ናዳ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ከ8 ሚሊዮን በላይ የብር እና ቁሳቁስ የሰብአዊ ድጋፍ አደረገ ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ በጎፋ ዞን፤ በገዜ ጎፋ ወረዳ ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝድ ቀበሌ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖቻችን ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተላከውን የመጀመሪያ ዙር የሰብአዊ ድጋፍ ቁሳቁስ ፣ መድኃኒት እና የድንገተኛ ህክምና ቡድን ( Emergency Management team ) ያካተተ የድጋፍ ቡድን ወደ ስፍራው ደርሰዋል ።
በሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
ዶ/ር ዳመኔ ደባልቄ እና በሲዳማ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽኔር በአቶ አበራ ዊላ የሚመራ ቡድን ነው በዛሬው ዕለት ወደ ስፍራው ደርሰው ተጎጅዎችን ለመደገፍ ከክልሉ መንግስት የተላከውን ድጋፍ ለዞኑ የስረከበው ።
በክልሉ መንግስት ለተጎጂው ህብረተሰብ የተላከውን በብር 5,000,000 እና በአይነት የ3,000,000 ፤ የምግብ እህል ፣ የምግብ ዘይት ፣ መድኃኒት ፣ የንጽህና መጠበቂያ ሳሙና ፣ አልባሳት ፣ ፍራሾች እና መሰል ቁሳቁሶች በድምሩ ከ8,000,000 ብር በላይ የሚሆን ድጋፍ የክልሉ ተወካይ ዶ/ር ዳመኔ ደባልቄ ለደቡብ ኢት/ህዝቦች ክልል ፕሬዝደንት ለክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ አስረክበዋል። ክቡር ፕሬዝደንቱም በተጎጂ ወገኖቻችን ስም ሰለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ድጋፉን ያስረከቡት ዶ/ር ዳመኔ ድጋፉን ካስረከቡ በኋላ ባሰሙት ንግግር የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ወገኖቻችን ላይ በደረሰባቸው አደጋ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን የተሰማው መሆኑን በመግለጽ ለመጀመሪያ ዙር የክልሉ መንግስት የላከው ድጋፍ እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣይም ክልሉ እና የክልሉ ህዝብ ከጎናቸው እንደማይለዩ ቃል በመግባት ፈጣሪ መጽናናትን ይስጣችሁ ብለዋል።
የሲዳማ ሒብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት
ሐምሌ 19-2016 ዓ.ም
ሀዋሳ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *