Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ እና የተጠሪ ተቋማት የፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ሠራተኞች በብልፅግና ፓርቲ ንድፈ ሀሳብ ‘’ልሳነ- ብልፅግና’’ መፅሔት ላይ የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት መድረክ እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡

ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም የሲዳማ ክልል መንግሥት ጤና ቢሮ፤
“የጠንካራ ፓርቲ ግንባታና በሕዝብ ንቅናቄ ሁለንተናዊ ብልፅግና የማረጋገጥ ጉዟችን” በሚል አርዕስት የተዘጋጀው የብልፅግና ፓርቲ ንድፈ ሀሳብ የሆነው ልሳነ- ብልፅግና መፅሔት 1 ቁጥር 5 እትም ላይ የቢሮውና የተጠሪ ተቋማት አባልና ደጋፊ ሠራተኞች ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ።
የፓርቲው ልሳን ዕትሙ ያተኮረው የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ አቅጣጫችን ፣ የጠንካራ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሰረታዊ መመዘኛዎች፣ ጠንካራ ተቋማዊ አቅም የመፍጠር መሻታችንና የፓርቲያችን ሁኔታ እንዲሁም የፓርቲያችን ቀጣይ ተልዕኮዎችና ተግባራት በሚሉ አንኳር ዐምዶችና ጉዳዮች ትኩረት በማድረግ በጥልቀት ውይይት በመካሄድ ላይ ነው።
የውይይት መድረኩን ዓላማ በማስመልከት የማስጀመሪያ መልዕክት ያስተላለፉት የጤና ቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ የፓርቲውን አባል እና ደጋፊ ሠራተኞችን አቅም ለመገንባት እና በፓርቲያችን ላይ የጠራ ግንዛቤ እንዲኖር በፓርቲው ንድፈ ሀሳብ መጽሔት ላይ በየዓመቱ በሩብ እና በዓመቱ መጨረሻ ላይ ውይይት ሲደረግ እንደነበረ ጠቁመው ዛሬ ለውይይት የቀረበውም የብልፅግና ፓርቲ -ልሳን ከተቀመጠው አሠራሪ የሚነሳ እንደሆነ በመጠቆም ፤ ዋና አላማውም ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት ጠንካራ መንግስት እና ተቋማት እንዲፈጠሩ በማድረግ ህዝባችንን ከድህነት በማውጣትና ወደ ብልፅግና ለምናደርገው ጉዞ ስኬት ሠራተኞቹ የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ነው ብለዋል ።
በውይይት መድረኩ የቢሮውና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችም ተገኝተዋል ።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *