Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ዛሬ ጳጉሜ 4/2016 የህብር ቀን

” ኅብረት ለሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በሲዳማ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች ዕለቱ ተከብሮ ዋለ።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሲዳማ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ ፦ በኅብረት ስለሠራን ተቋማችን በዚህ ዓመት በክልሉ በሪፎርም ሥራዎች የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የዋንጫ ፣ የሜዳሊያ እና የምስክር ወረቀት መሸለሙን አንስተው ይህ ውጤት እንዲመጣ በትጋት የሰሩትን አጠቃላይ የኢንስቲትዩቱን ሰራተኞች አመስግነዋል።
ዶ/ር ዳመነ አክለውም ተቋሙ ከዚህ በኋላ ከሀገር አቀፍ አልፎ በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪ ተቋም እንዲሆን መሥራት አለብን ካሉ በኋላ አዲሱን ዓመት አስመልክተው ፦ አዲሱ ዓመት የስላም፣ የጤናና የብልፅግና እንዲሆንልን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል ።
የሲዳማ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ጳጉሜ 4/2016 ዓ.ም
ሀዋሳ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *