Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ የቅድመ መከላከል ስራ እየተሰራ ነው፡- ጤና ሚኒስቴር

*****************

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ የሚያስችሉ የቅድመ መከላከል ተግባራት በትኩረት እየተሰሩ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጉዳዩን በሚመለከት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በሰጡት መግለጫ፤ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ በዓለም የጤና ድርጅት የህብረተሰብ ጤና ስጋት መሆኑ ከተገለፀ ጀምሮ፣ በሽታው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ የቅድመ መከላከል ስራዎች በትኩረት እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ከዚህም መከካል በድንበርና በተመረጡ አካባቢዎች ላይ ቅኝት የማድረግ፣ የልየታ ስራ፣ በሽታውን መመርመር የሚያስችል የላብራቶሪ አቅምን የማሳደግ እንዲሁም የባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሚኒስትሯ አያይዘውም፤ እስከ አሁን ድረስ በኢትዮጵያ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የተያዘ ሰው አለመኖሩን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ኃይሉ በበኩላቸው፤ በሽታው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
እስከ አሁን ድረስ በ13 አፍሪካ ሀገራት የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ መከሰቱን ከጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *