Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ክስተት አስተዳደር ስርዓት (Regional Incident Management System) በክልሉ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (PHEOC) ሥራዎች በዛሬዉ ዕለት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተገምግሟል፡፡

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ፣ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በክልሉ አንዳንድ አከባቢ የተከሰቱ የኮሌራ ወረርሽኝ እና የወባ በሽታ ስርጭት ያለበት ደረጃ ተገምግሟል፡፡
መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊዋ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ሲሆኑ ከክረምት ጋር ተያይዞ አንዳንድ ወረዳዎች የተከሰቱ የኮሌራ ወረርሽኝ እና የወባ በሽታ ስርጭት ከሚጠበቀዉ በላይ መሆኑ አሳሳቢ የህብረተሰብ ጤና ስጋት እየሆነ ቢመጣም ከጤና ቢሮ፣ ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እስከታች ድረስ ወርደዉ የሚደግፉ የባለሙያዎች ቡድን በማዋቀር ጠንካራ ድጋፍ፣ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ በአሁኑ ወቅት የመቆጣጠር ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በውይይት ወቅት እንዳሳሰቡት አሁን እየቀነሰ ያለዉ የኮሌራና የወባ ወረርሽኝ የጠንካራና ብርቱ ክትትል ዉጤት ቢሆንም ከክረምት ወቅት ጋር ተያይዞ እንደገና ሊጨምር ስለሚችል መዘናጋት ሳያስፈልግ ከወትሮ ይልቅ ብርቱ ድጋፍና ክትትል እንደሚያስፈልግ ገልፆዋል፡፡ በተጨማሪ እስከታች ድረስ ወርደዉ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ እየደገፉ ያሉ ባለሙያዎችን በቅድሚያ አመስግኗል፡፡
ከዉይይቱ ተሳታፊዎች እና ድጋፍ የሚያካሂዱ ቡድኖች በርካታ ሙያዊ አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት በርካታ ተግዳራቶች ቢኖሩትም ለመቆጣጠር ጠንክረዉ እየሰሩ እንደሆነ ገልፆዋል፡፡ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ በሽታዎች በተከሰቱባቸው አካባቢዎች ጥቅት የግብዓት እጥረት በስተቀር በበቂ ሁኔታ እያዳረሰ መሆኑን የክልሉ መድኃንት አቅርቦት አገልግሎት (EPSS) ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘመን ለገሰ ገልፆዋል፡፡ የደረሱ መድኃንቶች ከጤና ተቋማት ወደ ዉጭ እንዳይወጡ ጠንካራ ቁጥጥርና ኦዲት እየተደረገ ክፍተት በታየበት እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ የክልሉ ጤናና ጤና ነክ ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ቡርሶ ቡላሾ አሳስቧል፡፡
በአጠቃላይ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን፣ ቅኝትና ምላሽን ለመደገፍ፤ በዞን፣ በወረዳ እና በጤና ተቋማት ደረጃ የድንገተኛ ክስተት አስተዳደር (incident Management system) ሥርዓትን እንደ መደበኛ ሥራ አድርገዉ በየቀኑ እየገመገሙ፣ በየደረጃው የተጋላጭነት ዳሰሳ ጥናት እያካሄዱ፣ የበሽታ ቅኝት እና ምላሽ ተግባራትን አቀናጅቶ በመስራት እንዲሁም የማህበረሰቡን ተሳትፎ በማጠናከር ሁሉም በየደረጃዉ የሚገኙ መዋቅሮች የትኩረት አጀንዳ አድርገዉ መሥራት እንደሚገባቸዉ አሳስበዋል።
የሲዳማ ክልል ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት የህዝብ ግንኙነት ዳይረክቶሬት
መስከረም 27/2017 ዓ.ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *