Skip to content የሲዳማ ክልል የሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሲዳማ ክልል ማረምያ ኮሚሽን በበጀት ዓመቱ በሀዋሳ እና በይርጋለም ለሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከክልሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ኃላፊ ከተከበሩ ከአቶ ማቶ ማሩ እና ከማረሚያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ከተከበሩ ኮንታሞ ቡርቃ እጅ የዋንጫና የዕውቅና ሽልማት አግኝቷል።
ይህ ውጤት እንዲመጣ ተቋሙን በእውቀት በመምራት በሳል አመራር በመስጠት ትልቅ ሚና የተጫወቱን፦ የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል የሆኑትን የተከበሩ ዶ/ር ዳመኔ ዳባልቄን እና የኢንስቲትዩቱ የማኔጅመንት አባላትን፣ባለሙያዎችን፣አጋር አካላትን እንዲሁም እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ የሚገኙትን ሁሉንም ባለድርሻ አካላትን እንኳን ደስ አላችሁ ልንል እንወዳለን ።
የሲዳማ ክልል ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት የህዝብ ግንኙነት ዳይረክቶሬት
መስከረም 21/2017 ዓ.ም
ሀዋሳ
- by admin
- on October 2, 2024
0