Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ከሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጤና ኢንስቲትዩት አደረጃጀት ዙሪያ የልምድ ልውውጥ አደረገ።

ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተወጣጡ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች በክልላቸው የሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ለማደራጀት በዛሬው ዕለት ወደ ሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት በመምጣት ተሞክሮ የመቅሰምና የስራ ልምድ ልውውጥ አድርገዋል ።

የልምድ ልውውጥ ቡድን አባላት በኢንስቲትዩቱ እየተተገበሩ ያሉትን የጤና መረጃ አያያዝ ሥርዐት ፣ የነፃ ስልክ ጥሪ ማዕከልን፤ እንዲሁም የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ፣ የሕብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ እና የጤና ምርምርና ተክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬቶችንና አጠቃላይ በተቋሙ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች ተመልክተዋል።

በመጨረሻም ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ከባለፈው ዓመት ወዲህ የዛሬው ለ5ኛ ጊዜ የተደረገ ጉብኝት መሆኑን አስታዉሰው ከዚህ በፊት የጋምቤላ፣ የአፋር ፣የትግራይ ክልሎች፣እና የአዲስ አበባ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የልምድ ልውውጥ ማካሄዳቸን ጠቅሰው ኢንስቲትዩታችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እና አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መምጣቱን እንደሚያሳይ ገልጸው አሁንም ተቋሙን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እንስራለን ብለዋል።

የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት

ሲዳማ/ሀዋሳ

19/02/2017 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *