ዛሬ በስልጠና ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የብልግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ስርአት ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ካሣ ስልጠናው ለሀገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚያግዝ መሆኑን በማንሳት ከዚህ በፍት በህዋስ ተደራጅታችሁ የነበራችሁ ዛሬ እራሳችሁን ችላችሁ መሠረታዊ ድርጅት በመሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመኔ ደባልቄ ክቡር እንግዳውን በማመስገን ሠራተኛው የተሰጠዉን ስልጠና በተግባር ላይ በማዋል እና የተሰጠንን የመሠረታዊ ድርጅት ደረጃን በግንባር ቀደምትነት መወጣት አለባችሁ በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል።
በተጨማሪም በማጠቃለያው መርሀ ግብር ላይ የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መሠረታዊ ድርጅት በማቋቋም እና የመሠረታዊ ድርጅቱን አመራሮችም በመምረጥ በደማቅ ሁኔታ ተጠቃሏል።
የሲዳማ ክልል ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሕዳር 04/2017 ዓ.ም
ሀዋሳ
All reactions: