_____________________//________________________________________
የኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመኔ ደባልቄ በተገኙበት የቢሮዉ አመራሮች፣ማናጅመንትና ባለሙያዎች በጎርቼ ወረዳ ሙራንቾ ጉንጮና ሀርቤ ምቃና ቀበለ ለአቅመ ደካማና የተቸገሩ ወገኖችን የመርዳት በጎ አድራጎት ተግባር ተከናዉነዋል።
የበጎነት እሳቤን በተግባር በማሳየት አርአያ ሊሆን የሚገባ ተግባር መፈጸም ተገቢ ነዉ ያሉት ዋና ዳይሬክተር በወረዳ አቅም ላጡ አቅመ ደካማ የሁለት ቤተሰብ ያረጁ ቤቶችን በማፍረስ አዲስ ቤት ለመገንባት መሠረት ጥለዋል።
ሰዉ ተኮር እሳቤ የሰነቀዉ ፓርቲያችን ብልጽግና የተቸገሩትንና አቅመ ደካማ ወገኖችን የመርዳት ተግባራትን ለመፈጸም ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት እየተፈጸመ ያለዉ የበጎነት ተግባር ዛሬ በጎርቸ ወረዳ ተገኝተን ችግር ዉስጥ ያሉ ወገኖቻችንን መርዳት አስችሎናል ብለዋል።
አክለውም የክልሉ መንግስት በፓርቲዉ መሪነት ስምንት እንሸትቮችን በማዘጋጀት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መገባቱን ያስታወሱት ዶ/ር ዳመኔ ዳባልቄ ከኢንሸቲቮቹ አንዱ የሆነዉ በጎ አድራጎት ተነሳሽነት /Charity initiative/ በሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ተግባራዊ ማድረግ ከተጀመረ ይህ 4ተኛ ዓመት መሆኑን ጠቁመዋል።
አያይዘዉም ሁሉም ሰራተኛ በየወሩ ከደመወዙ በመቁረጥና ይህንን የሚያስተባብር ኮሚቴ በመሰየም በተጀመረዉ አዎንታዊ እንቅስቃሴ ከዉስጥም ሆነ ከቢሮ ዉጭ የተቸገሩትን መርዳት፣ የአቅመ ደካማ ወገኖች ቤት በማደስና አዲስ ሰርቶ በማስረከብ፣ ለወላጅ አልባ ህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ የመስጠትና ሌሎችም የተጀመሩ በጎ ተግባራት መቀጠል አለባቸዉም ብለዋል።
የጎርቸ ወረዳ አስተዳደር ተወካይ አቶ ቱቻ ቱምቻ በበኩላቸው በቢሮዉ አመራሮችና ባለሙያዎች እየተፈጸመ ያለዉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መልካም ስራና በጎነት በአርአያነት እንደሚጠቀስ ተናግረዉ በተደረገዉ መልካም ተግባር ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።
በተለይም ደግሞ በቢሮዉ ሠራተኞች መካከል በጎነትንና አብሮነትን የሚያጸኑ፣ የመተጋገዝ እሳቤን የሚያጎለብቱ ተግባራትን በንቃት በማከናወን አርአያነትን እያስመሰከሩ ያሉ ተግባራት እየተፈጸሙ ስለመሆናቸዉ ተገልጿል።
የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት
ጥቅምት21/2017ዓ.ም
ሀዋሳ
All reactions:
27Yoel Yoola, Sidama Public Health Institute Communication Affairs and 25 others