Skip to content የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመኔ ደባልቄ በመድረኩ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ዘርፈ-ብዙ ተግባራት እንደተተገበሩ ገልፀው የወባ ጫናን ለመቀነስና ለመከላከል ከአካባቢ ቁጥጥር ስራ ባለፈ ሕብረተሰቡ የፀረ-ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭትንና የአልጋ አጎበርን በአግባቡ መጠቀም እንዳለበት ገልፀዋል።
በመቀጠልም የሪፖርት ሙሉዕነትንና ወቅታዊነት በመጠበቅ ፣ የግምገማ እና ግብረ መልስ ስርዓትን በመዘርጋት እና ተቋማዊ አንድነትን ማጠናከርን ባህል ማድረግ ይገባል ያሉት ዋና ዳይረክተሩ በ4 ወር ውስጥ ያልተፈፀሙ ተግባራትን በመለየት ጊዜ ሰጥቶ መስራት ተገቢ መሆኑን አሳስበዋል።
አክለውም ኢንስቲትዩቱ ጥሩ በሚባል ደረጃ ያከናወናቸው ተግባራት አበረታች በመሆናቸው የተጀመሩ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከር የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
በተጨማሪም የጤና ኢንስቲትዩቱ በክልሉ ተከስቶ የነበረውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመከለካልና ለመቆጣጠር ህዝቡንና አጋር ድርጅቶችን በመቀናጀት ወረርሽኙን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማስቆም የቻለ መሆኑንና የተሰራው ስራ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በኢንስቲትዩቱ የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ደሳለኝ የ4 ወር የቁልፍና የአበይት ተግባራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የተያዙ አዳዲስ እርምጃዎችን እና የቀጣይ ተግባራትን በተመለከተ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት ከዚህ የበለጠ ርብርብ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ዋና ዳይሬክተሩ እና ምትክል ዋና ዳይሬክተሩ የተለያዩ አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት የተጀመሩትንም ተግባራት በተገቢው በማጠናከር የቁልፍ ተግባራት አመላካቾች ላይ ትኩረት አድርጎ መፈጸም እንደሚገባ ገልጸዋል።
አፈፃፀማቸው ዝቅተኛ የሆኑትን ተግባራት በመለየትና ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመስራት የተጀመሩ ተግባራትን በማጠናከር እንዲሁም በክልሉ ላይ ተፅዕኖ እየፈጠሩ ያሉ በሽታዎችን በመለየት፣ችግር ፈቺ ጥናት በማካሄድ የማህበረሰብ-አቀፍ ቅኝት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንሚገባ አሳስበዋል።
ሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት
ህዳር 28/2017 ዓ.ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን በነፃ የስልክ መስመር -7794 በመደወል ያግኙ !!
- by admin
- on December 12, 2024
0