Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የተቀናጀ ድጋፍዊ ክትትል ቡድን በሲዳማ ክልል የጤና ተቋማትን የስራ እንቅስቃሴና የወባ በሽታ የመከላከል ስራ ላይ የማህበረሰቡን ተሳትፎ በመዘዋወር ምልከታ አድርጓል

__________

በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ የተመራው የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ቡድን የጤና ተቋማትን የስራ እንቅስቃሴና የወባ በሽታ መከላከል ላይ እየተሰራ ያለዉን የማህበረሰቡን ተሳትፎ ቃኝተዋል።

በድጋፋዊ ምልከታቸውም የክልሉ ጠቅላላ ላቦራቶሪ ፣ የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ጤና ዳይሬክቶሬት ፣ አዳሬ እና ይርጋዓለም ጠ/ሆስፒታሎች፣ ወንዶ ገነት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ የወንዶገነት ወረዳ ጤና ጽ/ቤት፣ ወሻ ጤና ጣቢያን እና በእነዚህ ስር የሚኙ ሁለት ጤና ኬላዎችንና ወደ አሥር አባወራ/እማወራ ደረጃ የተመለከቱ ሲሆን ጤና ተቋማት ለታካሚ እየሰጡ ያሉ የሕክምና አገልግሎት፣ በወባ መከላከልና ቁጥጥር ዙሪያ ያለውን አገልግሎትና የማህበረሰብ ተሳይፎ በመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ አሃድ ሊሰራ የሚገባ የተቀናጀ ስራ እንዲሁም ትስስር ሁኔታን በሚመለከት ባለፉት ጊዜያት የተሰሩ ስራዎችን በጥልቀት ተመልክተው ገምግመዋል።

በድጋፍና ክትትሉ የተለዩ ጠንካራ ጎኖች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና የተስተዋሉ ጉድለቶችንም በሚቀርፍ ሁኔታ ላይ ዉይይት ተደርጓል።

Website: moh.gov.et

Facebook: Ministry of Health,Ethiopia

Twitter: x.com/fmohealth

YouTube: @FMoHealthEthiopia

Tiktok: moh ethiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *