Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ሁሉም የክልሉ የጤና ተቋማት ጥራት ያለው የላቦራቶሪ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል በብሔራዊ ደረጃ የሚቀረፁ የተለያዩ የጥራት ማሻሻያ ፕሮግራሞችን የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ቀጣይነት ያለው የጤና ላቦራቶሪ ልማት እንዲኖር ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሀናጋ።ከታህሳስ 21-26/2017ዓ/ም ድረስ የተሰጠው ስልጠና ተጠናቋል።

የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ታህሳስ 26/2017ዓ.ም

በማጠቃላው ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሀናጋ ሁሉም የክልሉ የጤና ተቋማት ጥራት ያለው የላቦራቶሪ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል በብሔራዊ ደረጃ የሚቀረፁ የተለያዩ የጥራት ማሻሻያ ፕሮግራሞችን የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ቀጣይነት ያለው የጤና ላቦራቶሪ ልማት እንዲኖር ተግባራዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል ።

አክለውም የህክምናን ጥራት ለመጠበቅ የላቦራቶሪ ድርሻ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ከስልጠና ባገኙት እውቀት ህብረተሰብን በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በኢንስቲትዩት የላቦራቶሪ ዳ/ዳይሬክተር አቶ አዳቶ አዴላ በበኩላቸው በየጤና ተቋማት የሰጡ ምርመራዎች ጥራታቸውን የጠበቁ እንድሆኑ የጀመርነውን የአቅም ግምባታ ስራ እንቀጥላለን ብሏል በመቀጠልም የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት በላቦራቶሪ አቅም ግንባታ ላይ ዘርፈ ብዙ ስራ እየሰራ መቆየቱን ገልጾ በዝህ ዙር ከ44 ጤና ተቋማት ለተወጣጡ ለ52 ባለሙያዎች በComprehensive (CD4,TB LF LAM,Crag and Dual HIV/syphilis) ምርመራ ላይ ስልጠና እንደተስጠ አስታውቋል።

የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት
ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም
ሀዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *