Skip to content በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ የገና በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ በመልካም ምኞት መልዕክታቸው ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን ካሉ በኋላ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ከሰማይ ሰማያት ወርዶ በድንግል ማርያም ማኅፀን ተፀንሶ ስለ እኛ ሲል በከብቶች በረት በመወለድ የአዲስ ተስፋ ጅማሮ የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ ሆኖልናል ብለዋል።
አክለውም የዘንድሮውን የገና በዓል የምናከብረው በዓሉ የሰላም የጤና እና የመተሳሰብ እንዲሆን እየተመኘን በበዓሉ ወቅት ለጤናዎ ይበልጥ ጥንቃቄ በማድረግ በተለይም ቅባቶችን በብዛት ከመመገብ እና ምግብን በደንብ ሳያበስሉ በመመገብ የጤና እክል እንዳይገጥመን ፣ ቅባቶችን መጥኖ በመመገብ እንዲሁም ምግብን በደንብ አብስሎ በመመገብ ጤናዎን እንዲጠብቁ ካሳስበ በኋላ ለሚገጥማችሁ ማንኛውም የጤና እክል በገጥም ተቋሙ ህዝቡን ለማገልገል 24 ሰዓት አገልግሎት ላይ መሆኑን ገልጾ 7794 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል አስፈላጊውን መረጃ እንዲያገኙ አሳስቧል ።
በመጨረሻም የዘንድሮው የገና በዓል ለክልሉ፣ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የአብሮነትና የብልጽግና እንዲሆን ተመኝተዋል።
ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ
የሲ/ብ/ክ/መንግስት ሕብረተስብ ጤና ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል
ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/
- by admin
- on January 14, 2025
0