Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የልጅነት ልምሻ (የፖሊዮ )መከላከያ ክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል ።

የካቲት 14/2017 የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት

ዕድሜያቸው ከ 5 አመት በታች ለሆናቸው ህፃናት ከየካቲት 14-17/2017ዓ.ም የሚሰጠው የመጀመሪያው ዙር የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ይፍዊ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በሲዳማ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በሚገኘው በቡልቻ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ተከናውኗል ።

የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በክትባት ዘመቻው ማስጀመሪያ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በጤናው ሴክተር መከላከልን መሰረት ባደረገው የጤና ፖሊሲ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከልና መቆጣጠር ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው በዚህም የፖሊዮን በሽታን በመከላከል አንዱ ነው ብለዋል።

ከዛሬው መርሃ ግብር ጋር በተያያዘ የፖሊዮ መከላከያ ክትባት በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች ተደራሽ እንደሚደረግ እና ከ1 ሚሊዮን በላይ ህፃናት ክትባቱን እንደሚወስዱም ተናግረዋል ።

የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በበኩላቸው ፥ የፖሊዮ በሽታን እንደ ሀገር ለማጥፋት በርካታ ተግባራት መከናወናቸው ውጤቶችም መመዝገብ መቻላቸውን ገልፀው ይሁን እንጂ የፖሊዮ በሽታ ባለመገታቱ ክትባቱን መስጠት እንዳስፈለገ ገልፀዋል ።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም እንደ ሲዳማ ክልል የተከሰተ የፖሊዮ በሽታ ባይኖርም እንደ ሀገር በክልላችን አጎራባች አከባቢዎችም በመከሰቱ ክልላችንን ጨምሮ በአሥር ክልሎች ክትባት ለመስጠት መታቀዱን ገልጸዋል።

ህፃናት ክትባት በወቅቱ መከተብ መብታቸው ወላጆችም ማስከተብ ግዴታቸው መሆኑን በመግለፅ
ለተቀናጀ ክትባት ዘመቻው ውጤታማነት ወላጆች/ አሳዳጊዎች መላው የህብረተሰብ ክፍል አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ዶ/ር ደመነ ደባልቄ ጥሪ አቅርበዋል ።

በይፍዊ የማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፕሬዚዳንት ፅ/ቤት የማዕበራዊ ዘርፍ ጉዳዮች አማካሪ ክቡር አቶ ባጥሶ ዌዲሶ፣ የክልሉ ምክር ቤት ማህበራዊ እና የሴቶችና ህጻናት ጉ/ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ አየለች ሌዳሞ ፣የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ፣ የክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ፣የቢሮው የማኔጅመንት አባላት ፣ የጤና ልማት አጋር ድርጅቶች፣ የቡልቻ ጤና ጣቢያ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያ ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
የካቲት 14/2017ዓ/ም
ሀዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *