
ከተጎበኙት ተቋማት መካከል በሀዋሳ ከተማ የሚገኘው የሚሊኒየም ጤ/አ/ጣቢያ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ሥራ እየተመራ ያለበትን አሠራር ፣ በኢንስቲትዩቱ የድጂታል ላይብራሪ እና በመስሪያ ቤቱ ህንጻ ላይ እየተተገበረ የሚገኘው የጽዱ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ይገኙበታል።
ከ20 በላይ የሚሆኑ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትን እና ሌሎች ከየክልል ቢሮዎች እንዲሁም ከፌደራል መ/ቤቶች የተወጣጡ ተሳታፊዎችን ያካተተው ጉብኝት ላይ የነበሩ እንግዶች በክልሉ ጤና ኢንስቲትዩት ለተሞክሮ የሚሆኑ ሥራዎች መሠራታቸውን በሰጡት አስተያየት ከመግለጻቸውም በላይ ዕድሉን አግንተው ይህን ምርጥ ሥራ መጎብኘታቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል ።
የማይበገር የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ስርዓት ለብሄራዊ ጤና ደህንነት !
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲዩት
የካቲት 1/2017 ዓ.ም
ሐዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/












