
የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በክልላችን ስር የሚገኙ ተቋማት ላቦራቶሪ የአለም አቀፍ የጥራት እና ቁጥጥር ስታንዳርድ በከተል እንድመረምሩ በርካታ ስራ እየሰራ ይገኛል።
ከዚህ በፊት ስተገበር የነበረው ISO 15189:2012 ወደ ISO 15189:2022 ስለተቀየረ ከቀን የካቲት 3/2017ዓ/ም ጀምሮ 19 ጤና ተቋማት የላቦራቶሪ ሀላፊ እና ላቦራቶሪ ጥራትና ቁጥጥር ባለሙያ ወደ አንድ ማዕከል በመሰብሰብ ዶክመንቶቻቸውን የሚያዘጋጁበት መድረክ በሀዋሳ ከተማ ተካሄዷል።
በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የላቦራቶሪ አቅም ግምባታ ዳይሬክቶረት ዳይረክተር አቶ ዳንኤል መለሰ በቦታው ተገኝተው የጎበኙ ስሆን በበኩላቸው ከጤና ጣቢያ ጀምሮ እስከ ሆስፒታል ያሉ ተቋማት ጥራቱን የጠበቀ ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው እና የግል ተቋማትን አካትተው በዚህ ልክ መዘጋጀቱ አበረታች እንደሆነ ጠቅሷል።
በኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪ ዳ/ዳይረክተር አቶ አዳቶ አዴላ በበኩላቸው በክልላችን ስር የሚገኙ የመንግስትና የግል ተቋማት አድሱን ስታንዳርድ መተግበር እንዳለባቸው ገልጸው ተቋሞቻችንን በአድሱ ስታንደርድ እውቅና እንድያገኙ ሙያዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
የካቲት 10/2017ዓ/ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/



