Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ክቡራን እንግዶቻችን እንኳን ወደ ሲዳማ ክልል በሰላም መጣችሁ !!

በሲዳማ ብ/ክልላዊ መንግስት ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲትዩት አዘጋጅነት በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በነገው ዕለት የሚካሄደው የ10ኛዉ ሀገር አቀፍ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ (PHEM forum) ፎረም ተሳታፊ እንግዶችን የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ እና ማኔጅመንቱ በሀዋሳ አየር ማረፍያ በመገኘት አቀባበል አድርጎላቸዋል።

አቀባበል ከተደረገላቸው እንግዶች መካከል ፦ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽኔር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማሪያም ፣ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ እና ሌሎች የፌደራል እንግዶች ይገኙበታል።

በሌላ በኩል ሌሎች ከሁሉም የሀገርቱ ክልሎች የተጠሩ የፎረሙ ተሳታፊ እንግዶችንም የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኃላፊ እና ማኔጅመንታቸው አቀባበል እያደረጉ ይገኛሉ።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንተስቲትዩት
ጥር 29/2017 ዓ.ም
ሐዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *