Skip to content 
የዘመቻው የእስከአሁን አፈጻጸም አስመልክቶ በተደረገው ውይይት ላይ የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና እንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ዳባልቀ እንደገለጹት ባለፉት 4 ቀናት በዘመቻው ከ862835 ለሚሆኑት ህጻናት የፖሊዮ ክትባት ተደራሽ መደረጉን በመግለጽ ይህም የእቅዱን 106% ማሳካት ተችሏል ነው ያሉት።
ከክትባት ዘመቻው ጋር የተቀናጁ ትኩረት የሚሹ ተግባራት አፈጻጸም አበረታች ውጤት ተመዝግቦአል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ 2832 ህጻናትን ከክትባት አገልግሎት ጋር የማቆራኘት ስራ ተሰርቶዋል እንዲሁም የከፍተኛ የምግብ እጥረት ችግር ያለባቸውን 2200 ህጻናት በላይ ለህክምና ከጤና ተቋማት ጋር የማስተሳስሩ ሥራ የተሰራ ሲሆን 75 እግረ ቆልማማ ህጻናትን ለተጨማሪ ህክምና ልየታ ተደርጓል ብለዋል።
ዘመቻው ግቡን እንድመታ በየደረጃ ያሉት አመራር አካላት፣ አጋር ድርጅቶች ፣ ሱፐርቫይዜሮች፣ ጤና ባለሙያዎች፣ ሚዲያ ባለሙያዎች፣ ሀይማኖት ተቋማት፣የሀገር ሺማግሌወች እንድሁም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ላደረጉት አስተዋጽኦ ዋና ዳይሬክተሩ ምስጋና አቅርቧል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
የካቲት 20/2017ዓ/ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/
- by admin
- on March 20, 2025
0