Skip to content 
**********
በኮንጎ ሪፐብሊክ፣ ብራዛቪል እየተካሄደ ባለው 74ኛው የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መድረክ፥ ዶ/ር ፎስቲን ኤንግልበርት ንዱጉሊሌ ቀጣዩ የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር በመሆን ተመርጠዋል።
በታንዛኒያ አቅራቢነት የተወዳደሩት ዶ/ር ፎስቲን ኤንግልበርት ንዱጉሊሌ አባል ሀገራት ከሰጡት ድምጽ አብላጫውን በማግኘት ቀጣዩ የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር በመሆን ተመርጠዋል።
የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፥ ዶ/ር ፎስቲን ኤንግልበርት ንዱጉሊሌ የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናን በዳይሬክተርነት እንዲመሩ በመሰየማቸው “እንኳን ደስ አለዎት” ብለዋቸዋል።
ጤናማና አምራች አህጉር እንድትኖረን ኢትዮጵያ ከዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ትብብር እና ድጋፏን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉም አረጋግጠውላቸዋል።
- by admin
- on September 30, 2024
0