Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የሲዳማ ክልል ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት በዛሬው ዕለት የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2017 ዓ.ም. ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ።

የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት በ2016 በጀት ዓመት የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ሲሆኑ በንግግራቸውም የኅብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎችን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የተሰሩ በርካታና ዘርፈ-ብዙ ሥራዎች ከክልሉም አልፎ በሀገር-ዐቀፍ ደረጃ ለምርጥ ተሞክሮ የሚሆኑ መሆኑን ገልጸዋል ።
ኃላፊዋ አክለውም የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት በድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ፣ ቅድመ-ዝግጅት ና ምላሽ አሰጣጥ ዙሪያ በተለይም ወረርሽኝን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር ከኢንስትቲዩት አንስቶ እስከ ኀብረተሰቡ ድረስ የሚሠሩ ሥራዎችን ለመተግበር የተቀናጀ አሠራር መፍጠሩ ለውጤቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዉ ፤ በሌላ በኩል ደግም የህዝባችንን የጤና ችግሮች በጥናትና በምርምር ለመፍታት ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀትና ስምምነት በመፈራረም በተናጠልም ሆነ በጋራ በርካታ ጥናቶች መሰራታቸውን ጠቁመው በቀጣይም እነዚህ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው እና በሌላ በኩል ደግሞ የኢንስቲትዩቱ ኀብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪው በክልሉ ውስጥ በጤና ተቋማት የሚገኙ ላቦራቶሪዎች ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጡ የተሠራው ሥራ ለአብነት የሚጠቀስ መሆኑንም ገልጸዋል ።
ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ የሲዳማ ኀብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደይሬክተር ጀነራል በበኩላቸው የክብር እንግዶችንና ጥሪ የተደረገላቸውን የስብሰባውን ተካፋዮች በሙሉ እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ በ 2016 በጀት ዓመት የኢንስቲትዩቱን ተልእኮ ለማሳካት በተቋሙ በሁሉም ዳይሬክቶሬቶች በዋናነት በኅብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በኩል ድንገተኛ አደጋዎች እና ወረርሽኞች እንዳይከሰቱ የመከላከልና ከተከሰተም በአጭር ጊዜ የመቆጣጠር ሥራዎች መሠራታቸውን ፤ በጤና ጥናትና ምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት በኩል ለኅብረተሰቡ የጤና ችግሮች በሆኑ በሽታዎችና አደጋዎች ላይ መንስኤውን የመለየት እና መረጃን መሠረት ያደረገ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችሉ ጥናቶች መሠራታቸውን፤ በኅብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬት በኩል የወረርሽኝ መንስኤዎችን የማጣራት ፣ የላቦራቶሪ ጥራት የማስጠበቅና ደረጃቸውን የማሻሻል በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን፤ በመረጃ አስተዳደር፣ ትንተናና ሥርጭት ዳይሬክቶሬት ዘርፍ የ10 ዓመት የጤና መረጃዎች በመረጃ ቋት ውስጥ ማስገባት መቻሉ፣ የተቋሙን ድረገጽ በመክፈት መረጃ ለሚፈልጉ ተደራሽ መደረጉንና የጤና መረጃዎች እንይጠፉ Cloud ላይ መቀመጡን ገልጸዋል ።
በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ እንሠሩ የታቀዱ ተግባራት በተሳካ ሁኔታ በመከናወናቸው ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል ።
በዕለቱ የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የጤና ልማት ዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ደሳለኝ ሲሆኑ ከዕቅዱ አንጻር የተከናወኑ ሥራዎችን እና በቀጣይ መሻሻል የሚገባቸውን እንዲሁም ትኩረት መደረግ ያለባቸዉን በሚገባ ካቀረቡ በኋላ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ም/አፈ-ጉባኤ ክቡር አቶ ዘነበ ዘርፉ፣ የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ እና የሲዳማ ክልል ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ ሲሆኑ በውይይቱ ላይ ሌሎች እንግዶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ተገኝተዋል።
በመጨረሻም በግምገማው መድረክ ላይ ተገኝተው አስተያየት የሰጡት፦የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ክቡር አቶ ባጢሶ ዌድሳ፣ የክልሉ ማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ አየለች ሌዳሞ ፣ የሀዋሳ ቅርንጫፍ EPSS ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘመን ለገሠ ፣ የጤናና ጤና ነክ ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ቡርሶ ቡላሾ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ማኔጅመንት አባላት የዞኖች ማህበራዊ ዘርፍና የጤና ደስክ ኃላፊዎች፣ የወረዳ ጤ/ጥ/ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣የወረዳዎች የPHEM አሰተባባሪዎች ሲሆኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት መድረኩ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት
ጳጉሜ 02/2016 ዓ.ም
ሀዋሳ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *