
የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም
የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች የካይዘን ፍልስፍና እና ጤና እና ጤና ነክ መረጃዎችን በአንድ ቋት በመሰብሰብ፣ በማደራጀት እና በመተንተን ውሳኔ ሰጭ አካላት እንዲጠቀሙበት ለማስቻል ዙርያ ስልጠና ተሰጠ።
የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሀናጋ መድረኩን በንግግር በከፈቱበት ወቅት በጤናው ዘርፍ የመረጃ ስርዓትን ማዘመንና መረጃን በየደረጃው ለውሳኔ ለመጠቀም ግብ ተቀርፆ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ለውጦችን የምናመጣበት ቁልፉ መረጃ በመሆኑ መረጃ ሳይኖር የሚወሰኑ ውሳኔዎች እድገትን ሊያመጡ እንደማይችሉ ገልፀዋል።
አክለውም ም/ል ዋና ዳይሬክተሩ ኢንስቲትዩቱ ክልላዊ የጤና እና ጤና ነክ መረጃ ቅመራ፣ ትንተና እና አስተዳደር ማዕከል አቋቁሞ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው ሀገራዊ መነሻን መሰረት በማድረግ በክልል ደረጃ ኢንስቲትዩቱ ዋና ዘርፍ አድርጎ እየሰራበት እንደሆነ ተናግረዋል::
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የገለፁት ም/ል ዋና ዳይሬክተር መረጃ ከሃብት በላይ እንደሆነ ተገንዝበን ትክክለኛ መረጃ በመስጠትና ተባብሮ በመስራት ሁሉም ሠራተኛ የበኩሉን እንደሚወጣ አሳስበዋል።
በመድረኩ የህብረተሰብ ጤና መረጃ ምንነት እና አሰራር ዙሪያ አቶ ሳንባቶ ካይሞ እና የካይዘን ፍልስፍና በተመለከተ አቶ ተክለ ሀ/ማረም ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን ከመድረኩ ተሳታፊዎች ሀሳብ እና አስተያየቶች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት
ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794



