
በዛሬው ዕለት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ለተለያዩ መንግስታዊ ስራ ጉዳዮች ወደ ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሲደርሱ በክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ እና በቢሮው ማኔጅመንት በሀዋሳ አውሮፕላን ጣቢያ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸዋል ::
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ክብርት ሚኒስትሯን እንኳን ደህና መጡ በማለት አቀባበል ካደረጉ በኋላ በክልሉ መልካም የቆይታ ጊዜ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ክብርት የጤና ሚኒስትሯ በክልሉ በሚቀጥሉት ቀናት በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ቆይታ እንደሚኖራቸው ተረጋግጧል ።
ሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ጥር 2/2017 ዓ.ም







