
ከትላንት ጀምሮ የተለያዩ አጀንዳዎችን ሲመሩ የቆዩት ክብርት የጤና ሚኒስትሯ በዛሬው ዕለት በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ጤና ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ጎብኝተዋል።
በዚህ ጉብኝት በክብርት ሚኒስትሯ የተጎበኙ ጤና ተቋማት መካከል የሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ፣ አዳሬ አ/ሆስፒታል ፣ ሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና የሚሊኒየም ጤና አ/ጣቢያ ይጠቀሳሉ ። በታዩት ጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች ፥ የበሽታ መከላከል ስራዎች ፣ የሕክምና አገልግሎቶች ፣ የተለያዩ ሪፎርሞች አተገባበር እና በአባወራ/እማወራ ደረጃ ቤት ለቤት የሚሰራው የቤተሰብ ጤና ቡድን ( FHT) አተገባበር በሚመለከት ክብርት ሚኒስትሯ በታዩት መልካም ጎኖች ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ ፤ መልካም ጎኖቹ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በመጨረሻም በየተቋማቶቹ ስለተደረገላቸው ገለጻ ክብርት ሚኒስትሯ አመስግነዋል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ጥር 3/2017 ዓ.ም





