Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ሲ/ብ/ክ/መንግስት ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ለሁለት አቅመ ደካማ ቤተሰብ ያስገነባውን ቤት አስረከ።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትን ሲያስገነባ የቆየዉን ቤት በማጠናቀቅ አስረከበ።

በቤት ርክክብ መርሀግብር ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ስናገሩ እነኝህ ቤተሰቦች ቀደም ስል እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ፀሀይና ዝናብ እየተፈራረቀባቸዉ ከልጆቻቸዉ ጋር እየኖሩ መቆየታቸዉን ጠቅሰዉ በኢንስቲትዩቱ አመራርና ሰራተኞች በተደረገላቸዉ ትብብር ከዚህ ችግር ተላቀዋል ስሉ ገልፀዋል።

በርክክቡ ፐሮግራም ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የክልሉ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፍፁም በላይነህ በበኩላቸዉ ኢንስትቲዩቱ ባለፉት ተከታታይ አራት ዓመታት በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን መሰራታቸውን አመላክተዋል።

ብልጽግና ድሀንና የተቸገሩትን የሚደገፍ መደጋገፍ ፍሬ እንደሚያፈራ በማመን በሀገር ደረጃ ሰፋፊ ስራዎችን የሰራ ፓርቲ ነዉ ስሉ ተናግረዋል ።

አያይዘዉም እንደክልላችንም በመደጋገፍ በክልሉ ያሉ ሀብቶችን የተቸገሩ ቤተሰቦችን ለመርዳትና የተሻለ ኑሮ እንድኖሩ ለማድረግ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በተሰሩ ስራዎች ትልቅ ለዉጥ መምጣቱን ተናግረዋል።

የጎርቼ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ እና ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳንፍለ ዳንግሶ ኢንስቲትዩቱ በወረዳችን የሰራዉ ስራ እጅግ በጣም የሚያስመሰግን ታሪክ የማይረሳዉ ነው ብሏል።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት
ጥር 22/2017 ዓ.ም
ሀዋሳ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *