Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

በሲዳማ ብ/ክ/መ/ጤና ቢሮ 4ኛ ዙሪ የተቀናጀ የኮቪድ -19 ክትባት ዘመቻ ክልላዊ የማስጀመሪያ ሰነ ስርዓት የክልሉ እንግዶች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በአለታ ወንዶ ከተማ ተካሂዷል።

በማስጀመሪያው ፕሮግራም ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ ም/የቢሮ ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ኃላፊ የሆኑት አቶ በላይነህ በቀለ በንግግራቸው  በኮቪድ-19 ምክንያት በዜጎች ላይ  ከሚደርስባቸው ህመምና ሞት ለመከላከል ክትባት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው በመሆኑ  በ4ኛው ዙሪ ዕድሜያቸው 12 ዓመትና በላይ ለሆናቸው ለ623,000 ሰዎች የሚሰጥ ሲሆን ከዚሁ በተጓዳኝ  በርካታ  ልጃገረዶችን ለህመምና ሞት እየዳረገ የሚገኘውን የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባትም ለ183,289 ልጃገረዶች እንደሚሰጥ ገልጸዋል ።

በዚሁ ዘመቻ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ሌሎች ወሳኝ የሆኑ የጤና ችግሮች  የልየታ ስራዎችም የሚሰሩ ሲሆን ለአብነትም የምግብ እጥረት ያለባቸውን ልየታና ህክምና ፣ ፍስቱላ እና የማህጸን ውልቃት ልየታ ፣ ታሞ ህክምና ያላገኙትን ህጻናት የመለየትና ወደ ጤና ተቋም መላክ ፣ከ30-49 ዕድሜ ክልል ለሚገኙ ሰቶች የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ህክምና  ፣ ሁሉንም ዓይነት ክትባት ጨርሶ ያልወሰዱትን የመለየትና መከተብ እንዲሁም የአይን ሞራ ግርዶሽ ህመም ተጠቂዎችን የመለየትና ህክምና እንዲያገኙ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ መድረኩን በንግግር የከፈቱት ም/ጤና ቢሮ ኃላፊና የጤና ፕሮግራም ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ በላይነህ በቀለ ገልጸዋል።

የክትባት ዘመቻው ከሚያዝያ 17 -27 ድረስ በጤና ተቋማት ፣ በጊዜያዊ ጣቢያዎች ፣ በት/ቤቶች እና ቤት ለቤትም አስፈላጊነቱ በታመነባቸው አከባቢዎች እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን ግለሰብ ነዋሪዎችና ወላጆች ይህንኑ አውቀው አገልግሎቱን እንዲጠቀሙና ልጆቻቸውን እንዲያስከትቡ  ጤና ቢሮው ጥሪውን ያቀርባል።

          ኮቪድን በጋራ እንከላከል !!

የሲዳማ ሒብረተሰብ  ጤና ኢንሰቲትዩት

ሚያዝያ 17/2015 ዓ.ም

           ሀዋሳ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *