Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ዛሬ የካቲት 10/2016 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሲዳማ ክልል ጤና ብሮ ጋር በመሆን በክልሉ የተከሰተው የኩፍኝ በሽታ  ወረርሽኝ ስርጭት ያለበት ደረጃ ገምግሞ በቀጣይ ስርጭቱ ለማስቆም የሚያስችል አቅጣጫም አስቀምጧል ።

ዛሬ የካቲት 10/2016 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሥራ ክፍል ኃላፊዎች   ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ከሥራ ክፍል ኃላፊዎች ጋር በመቀናጀት በክልሉ ስር ከሚገኙ ከተለያዮ ወረዳዎች የተወጣጡ የጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ከአራቱም ዞን የማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊዎችና የጤና ክፍል ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በቀን የካቲት 10/2016 ዓ.ም በክልሉ የተከሰተው የኩፍኝ  በሽታ  ወረርሽኝ ያለበት  ደረጃ ገምግሞ  ደካማ ጎኑን በመለየት በቀጣይ  ወረርሽኙን  ለማስቀረፍ  ልሰራባችው የሚገባውን  ነጥባች  ላይ አቅጣጫ  አስቀምጧል፡፡

የተወያዩበት አበይት ጉዳዮች፡-

1.ለሕብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ መሆኑ ተጠቅሷል ።

2.ጠንካራ የሆነ ድጋፍና ክትትል መደረግ እንዳለበት በቀጣዩ እንደ መፍተሄ አቅጣጫ ተቀምጧል ።

3.የጤና ባለሙያ አቅም ማጎልበት በዝርዝሩ አቅጣጫ ላይ ተቀምጧል ።

4.ወረርሽኙን ለማስቆም ጠንካራ ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ  መቀጠልም እንዳለበት ተገልጿል ።

ምንጭ :- ከሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት

የካቲት 10/2016 ዓ/ም

    ሀዋሳ  ሲዳማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *