Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የህብረተሰብ ጤናን በዶክትሬት ደረጃ/ Doctor of Public Health (DOPH) የጤና ትምህርት መስጠት የሚያስችል ሀገር አቀፍ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን የህበረተሰብ ጤና ትምህርት፣ በዶክትሬት የትምህርት ደረጃ ለማስጀመር፣ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ልዩ ልዩ ምሁራን የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የሰው ሀብት ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰግድ ሳሙኤል እንደገለጹት፣ የጤናው ዘርፍ ብዙ እይታ የሚፈልግ ሴክተር ሲሆን የማህበረሰብ ጤና ጉዳይ በተሻለ ዕውቀትና ክህሎት መምራት እንዲቻል የህበረተሰብ ጤናን በዶክትሬት ደረጃ/ Doctor of Public Health (DrPH) ማስጀመር መቻሉ ትልቅ አቅም ይፈጥራል፡፡

ስራ አስፈጻሚው፣ ይህ በአፍሪካ በበርካታ ሀገራት የማይስተዋል የትምህርት መስክ መከፈቱና ምሁራንን ማሳተፉ ወደፊት እንደ ሀገር በሽታን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ረገድ የሚኖረው አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የትምህርት መስኩ እውን እንዲሆን በግል እና በተቋም ደረጃ የተጉ አንጋፋ ባለሙያዎችንና ከፍተኛ አመራሮችንም አመስግነዋል፡፡

የአዲስ ኮንቲኔንታል ኢኒስቲትዩት ኦፎ ፐብሊክ ሄልዝ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር የማነ ብርኃን በበኩላቸው፣ የህበረተሰብ ጤናን በዶክትሬት ደረጃ/ Doctor of Public Health (DrPH) ለማስጀመር ለዓመታት በርካታ ጥረቶች ተደርገው ሳይሳካ የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ የዚህ ፕሮግራም መጀመር ለሀገራችን የጤናው ዘርፍ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡

የማህበረሰቡን ጤና በመረዳትና ውስብስብ የጤና ችግሮችን መለየት እና መፍታት እንዲሁም ማህበረሰቡን ከወረርሽኝ እና ከተለያዩ የጤና ስጋቶች መታደግ የሚችል ባለሙያ ከማፍራት ረገድ ይህ ፕሮግራም ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማህበር ተወካይ አቶ ተስፋዬ ደምለው፣ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት፣ በዶክትሬት ደረጃ የሚሰጥባቸው የሀሮማያ እና የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መሆናቸውን ገልጸው ዩንቨርሲቲዎቹ፣ ካላቸው የዳበረ ልምድ፣ የተደራጀ ላብራቶሪ እና የሰው ኃይል አንፃር ብቃት ያላቸው የጤና ባለሙያዎችን ሊያፈሩ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ እና የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የትምህርት መስኩ ከመከፍት ጋር ተያይዞ ስለሚኖረው የስርዓት ትምህርት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ጽሁፍ አቅርበው ውይይት የተደረገ ሲሆን በመድረኩ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከሙያ ማህበራት፣ ከአጋር ድርጅቶች፣ ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት እና ከጤና ሚኒስቴር ከልዩ ልዩ ክፍሎች የተውጣጡ ባለሙያዎች ተገኝታዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *