Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ በአቶ ዳንኤል ዳምጤው የሚመራ ቡድን ከሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የልምድ ልውውጥ አድርጓል።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ከአዲስ አበባ ለመጡ ልዑካን ቡድን አባላት መልዕክት ከአስተላለፉ በኃላ በአጠቃላይ በኢንስቲትዩቱ ደረጃ የተሰሩ ሥራዎች ላይ ገለጻ ተደርጓል። በመቀጠልም እንግዶቹ በተቋሙ ከሚገኙ ዳይሬክተሮች አማካኝነት የሥራ ምልከታና ልምድ ልውውጥ አድርገዋል። በተጨማሪም የልዑካን ቡድን አባላት፤ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ፣ የጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና፣ የሕብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ ፣ የጥናትና ምርምር ስራዎችና ነፃ የስልክ መስመር አጠቃቀም ዙርያ በርካታ ምርጥ ሥራዎች እንደተሰሩ በአስተያየታቸው ገልጸዋል።

በክልላችን በሁለት ወር ውስጥ እደዚህ አይነት ልምድ ልውውጥ ሲካሄድ የዛሬው 3ኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ በፊት የጋምቤላና የአፋር ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የልምድ ልውውጥ ማካሄዳቸው ይታወሳል። ይህ የሚያሳው ኢንስቲትዩታችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እና አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መምጣቱን ያሳያል።

በመጨረሻም፥ ዶ/ር ደመነ እንደገለጹት በቀጣይነት ተቋማችን የልህቀት ማዕከል (Center of Excellence) ለማድረግ ተግተን እንሰራለን ብለዋል።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት

ሲዳማ/ሀዋሳ

14/07/2016 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *